ኢያሱ 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ትነግሯቸዋላችሁ፦ ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ፤’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስ በደረቅ ምድር ተሻገረ’ ብላችሁ ንገሯቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ምድር ላይ ተሻገረ፤’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ሕዝብ የዮርዳኖስን ወንዝ በደረቅ ምድር የተሻገሩበት ጊዜ መኖሩን ትነግሩአቸዋላችሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ተሻገረ፥ |
“የፈርዖን ፈረሶች ከሰረገሎቹና ከፈረሰኞቹ ጋር ወደ ባሕር ገቡ፤ እግዚአብሔርም የባሕሩን ውኆች መለሰባቸው፤ የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ መካከል በየብስ አለፉ፤ ውኃውም ለእነርሱ በቀኝ እንደ ግድግዳ፥ በግራም እንደ ግድግዳ ሆነላቸው።”
ባሕሩን ያደረቅሽ፥ ጥልቁንም ውኃ ያደረቅሽው፥ የዳኑትም ይሻገሩ ዘንድ ጥልቁን ባሕር ጥርጊያ ጎዳና ያደረግሽ አይደለሽምን?
ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀርያትያርም አውራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።
የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ የእስራኤል ልጆች ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ።
ኢያሱም ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፥ “ልጆቻችሁ፦ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው በሚጠይቋችሁ ጊዜ፥