ንጉሡም የፈረደውን ፍርድ እስራኤል ሁሉ ሰሙ፤ ፍርድን ለማድረግ የእግዚአብሔር ጥበብ በእርሱ ላይ እንደ ነበረ አይተዋልና ከንጉሡ ፊት የተነሣ ፈሩ።
ኢያሱ 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው፤ ሙሴንም እንደ ፈሩ በዕድሜው ሁሉ ፈሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያች ዕለት እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደረገው፤ ሕዝቡ ሙሴን እንዳከበሩት ሁሉ፣ ኢያሱንም በሕይወት ዘመኑ ሁሉ አከበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ጌታ ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው፤ ሙሴንም ይፈሩት እንደ ነበር እንዲሁ ኢያሱን በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ፈሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደረገው፤ ሙሴን ያከብሩት እንደ ነበር ኢያሱንም በሕይወቱ ዘመን ሁሉ አከበሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ኢያሱን በእስራኤል ሁሉ ፊት ከፍ አደረገው፥ ሙሴንም እንደ ፈሩ በዕድሜው ሁሉ ፈሩት። |
ንጉሡም የፈረደውን ፍርድ እስራኤል ሁሉ ሰሙ፤ ፍርድን ለማድረግ የእግዚአብሔር ጥበብ በእርሱ ላይ እንደ ነበረ አይተዋልና ከንጉሡ ፊት የተነሣ ፈሩ።
በኢያሪኮም የነበሩት የነቢያት ልጆች ኤልሳዕ ወደ እነርሱ ሲመጣ ባዩት ጊዜ፥ “የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ ዐርፎአል” አሉ። ሊገናኙትም መጥተው በፊቱ በምድር ላይ ሰገዱለት።
እግዚአብሔርም ሰሎሞንን በእስራኤል ሁሉ ፊት እጅግ አገነነው፤ ከእርሱ በፊትም ለነበሩት ነገሥታት ያልሆነውን የመንግሥት ክብር ሰጠው።
ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
እግዚአብሔርም በግብፃውያን ፊት ለሕዝቡ ሞገስን ሰጠ፤ አዋሱአቸውም፤ ይህ ሙሴም በግብፃውያንና በፈርዖን፥ በሹሞቹም ፊት እጅግ የከበረ ሰው ነበረ።
እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርም አመኑ፤ ባሪያውንም ሙሴን አከበሩ።
አንተ ሥራህን ታሳምር ዘንድ የእግዚአብሔር መልእክተኞች ናቸውና። ክፉ ብታደርግ ግን ፍራ፤ ሰይፍ የታጠቁም ለከንቱ አይደለም፤ ክፉ አድራጊዎችን ለመቅጣት የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸውና።
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር መሆኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእስራኤል ልጆች ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አደርግህ ዘንድ እጀምራለሁ።
ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጮኸ፥ እግዚአብሔርም በዚያ ቀን ነጐድጓድንና ዝናብን ላከ፤ ያንጊዜም ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርንና ሳሙኤልን እጅግ ፈሩአቸው።