La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 21:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞ​ችና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ለሌ​ዋ​ው​ያን በዕጣ ሰጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ እስራኤላውያን እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ባዘዘው መሠረት፣ እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያኑ በዕጣ መደቡላቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም በሙሴ አማካይነት እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሙሴ አማካይነት እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት የእስራኤል ሕዝብ እነዚህን ከተሞችና የግጦሽ ምድር ለሌዋውያን በዕጣ አካፈሉአቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም በሙሴ እጅ እንዳዘዘ የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰምርያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ።

Ver Capítulo



ኢያሱ 21:8
11 Referencias Cruzadas  

“ስም​ዖ​ንና ሌዊ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ናቸው፤ በጭ​ቅ​ጭ​ቃ​ቸ​ውና በጦ​ራ​ቸው ዐመ​ፅን ፈጸ​ሙ​አት።


ቍጣ​ቸው ርጉም ይሁን፤ ጽኑ ነበ​ርና፤ ኵር​ፍ​ታ​ቸ​ውም ብርቱ ነበ​ርና፤ በያ​ዕ​ቆብ እከ​ፋ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም እበ​ታ​ት​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።


የበደለኛ ሰው በደሉ ሁሉ ወደ ጕያው ይመለሳል። ጽድቅ ሁሉ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።


ዕጣ ክርክርን ያስተዋል፥ በኀያላንም መካከል ይለያል።


የሮ​ቤል ልጆ​ችና የጋድ ልጆ​ችም መጥ​ተው ሙሴ​ንና ካህ​ኑን አል​ዓ​ዛ​ርን፥ የማ​ኅ​በ​ሩ​ንም አለ​ቆች እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፦


ምድ​ሪ​ቱ​ንም ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ች​ሁም ትከ​ፋ​ፈ​ሏ​ታ​ላ​ችሁ፤ ለብ​ዙ​ዎች ድር​ሻ​ቸ​ውን አብ​ዙ​ላ​ቸው፤ ለጥ​ቂ​ቶ​ችም ድር​ሻ​ቸ​ውን ጥቂት አድ​ርጉ፤ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደ​ቀ​ለት በዚያ ርስቱ ይሆ​ናል፤ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ነገ​ዶች ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ።


ከተ​ሞ​ቹም ለእ​ነ​ርሱ መኖ​ሪያ ይሆ​ናሉ፤ መሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውም ለከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና ለእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው ይሁን።


እና​ን​ተም ምድ​ሪ​ቱን በሰ​ባት ክፍል ክፈ​ሏት፤ ወደ እኔም ወዲህ አም​ጡ​ልኝ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትእ​ዛዝ ከር​ስ​ታ​ቸው እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞ​ችና መሰ​ማ​ር​ያ​ቸ​ውን ለሌ​ዋ​ው​ያን ሰጡ​አ​ቸው።


ለሜ​ራ​ሪም ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው ከሮ​ቤል ነገድ፥ ከጋ​ድም ነገድ፥ ከዛ​ብ​ሎ​ንም ነገድ ዐሥራ ሁለት ከተ​ሞች ተሰ​ጡ​አ​ቸው።


የይ​ሁ​ዳም ልጆች ነገድ፥ የስ​ም​ዖ​ንም ልጆች ነገድ፥ የብ​ን​ያ​ምም ልጆች ነገድ በስ​ማ​ቸው የተ​ጠ​ሩ​ትን እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞች ሰጡ​አ​ቸው።