በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ካሉ ከመሰማርያዎቻቸው ጋር አርባ ስምንት ከተሞች ነበሩ።
ኢያሱ 21:42 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰማርያቸው ጋር ነበሩ፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ እንዲሁ ነበሩ። [ኢያሱም በየድንበሮቻቸው ምድርን ማካፈልን ጨረሰ። የእስራኤል ልጆችም ለኢያሱ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ድርሻውን ሰጡት፤ እርሱ የሚፈልጋትን ከተማ በኤፍሬም ተራራ የምትገኘውን ቴምናሴራን ሰጡት፤ ከተማም ሠራባት፤ በውስጧም ተቀመጠ። ኢያሱም በምደረ በዳ በመንገድ የተወለዱትን የገረዘባቸውን የድንጋይ ባልጩቶች ወስዶ በቴምናሴራ አኖራቸው።] አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው መሰማሪያዎች ነበሯቸው፤ መሰማሪያ የሌለው ከተማ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው በዙሪያቸው መሰማሪያዎች ነበራቸው፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ እንዲሁ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእነዚህም መሬቶች በእያንዳንዱ ዘሪያ የግጦሽ መሬት ነበራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰምርያቸው ጋር ነበሩ፥ እነዚህም ከተሞች ሁሉ እንዲሁ ነበሩ። |
በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ካሉ ከመሰማርያዎቻቸው ጋር አርባ ስምንት ከተሞች ነበሩ።
እግዚአብሔርም ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻቸው የማለላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤል ሰጠ፤ ወረሱአትም፥ ተቀመጡባትም።