ኢያሱ 21:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)41 በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ በእነዚህ ከተሞች ዙሪያ ካሉ ከመሰማርያዎቻቸው ጋር አርባ ስምንት ከተሞች ነበሩ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም41 እንግዲህ እስራኤላውያን ርስት አድርገው ከያዙት ምድር ለሌዋውያኑ የተሰጧቸው ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው በአጠቃላይ አርባ ስምንት ነበሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)41 በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰማሪያቸው ነበሩ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም41 በእስራኤላውያን ይዞታ ሥር የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ከግጦሽ መሬታቸው ጋር አርባ ስምንት ነበሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)41 በእስራኤል ልጆች ርስት መካከል የነበሩት የሌዋውያን ከተሞች ሁሉ አርባ ስምንት ከተሞችና መሰምርያቸው ነበሩ። Ver Capítulo |
እነዚህም ከተሞች እያንዳንዳቸው ከመሰማርያቸው ጋር ነበሩ፤ እነዚህም ከተሞች ሁሉ እንዲሁ ነበሩ። [ኢያሱም በየድንበሮቻቸው ምድርን ማካፈልን ጨረሰ። የእስራኤል ልጆችም ለኢያሱ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ድርሻውን ሰጡት፤ እርሱ የሚፈልጋትን ከተማ በኤፍሬም ተራራ የምትገኘውን ቴምናሴራን ሰጡት፤ ከተማም ሠራባት፤ በውስጧም ተቀመጠ። ኢያሱም በምደረ በዳ በመንገድ የተወለዱትን የገረዘባቸውን የድንጋይ ባልጩቶች ወስዶ በቴምናሴራ አኖራቸው።]