ኢያሱ 21:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ጠናሕንና መሰማርያዋን፥ ዬባታንና መሰማርያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምናሴ ነገድ፣ እኩሌታ ደግሞ ታዕናክና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሁለት ከተሞች ተሰጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰማሪያዋን፥ ጋት-ሪሞንንና መሰማሪያዋን፤ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምዕራብ ምናሴ ግዛት ተከፍለው የተሰጡአቸውም ሁለት ከተሞች ከግጦሽ ምድራቸው ጋር ታዕናክና ጋትሪሞን ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ታዕናክንና መሰምርያዋን፥ ጋትሪሞንንና መሰምርያዋን፥ ሁለቱን ከተሞች ሰጡአቸው። |
በይሳኮርና በአሴር መካከል ቤትሳንና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ፥ መጌዶና መንደሮችዋ፥ የመፌታ ሦስተኛ እጅና መንደሮችዋ ለምናሴ ነበሩ።
ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤ በዚያ ጊዜ በመጌዶ ውኆች አጠገብ በቶናሕ የከነዓን ነገሥታት ተዋጉ፤ በቅሚያም ብርን አልወሰዱም።