ኢያሱ 21:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓናቶትንና መሰማርያዋን፥ አልሞንንና መሰማርያዋን፤ አራት ከተሞችን ሰጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዓናቶትና አልሞን የተባሉትን አራት ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አናቶትንና መሰማሪያዋን፥ አልሞንና መሰማሪያዋን፤ አራት ከተሞችን ሰጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐናቶትና ዐልሞን ተብለው የሚጠሩት ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አናቶትንና መሰምርያዋን፥ አልሞንና መሰምርያዋን፥ አራት ከተሞችን ሰጡ። |
ንጉሡም ካህኑን አብያታርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፥ አባቴም የተቀበለውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀበልህ አልገድልህምና በዓናቶት ወዳለው ወደ እርሻህ ፈጥነህ ሂድ” አለው።
ከብንያምም ነገድ ጌባንና መሰማርያዋን፥ ጋሌማትንና መሰማሪያዋን፥ ዓናቶትንና መሰማሪያዋን ሰጡ። ከተሞቻቸው ሁሉ በየወገናቸው ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
በብንያም ሀገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት ወገን ወደ ሆነ ወደ ኬልቅያስ ልጅ ወደ ኤርምያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል።