ኢያሱ 2:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቷም በከተማ ቅጥር የተጠጋ ነበረና፥ እርስዋም በቅጥሩ ላይ ተቀምጣ ነበርና በመስኮቱ በገመድ አወረደቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኖሪያ ቤቷ የከተማውን ቅጥር ተጠግቶ የተሠራ ስለ ነበር፣ ሰዎቹን በመስኮት አሾልካ በገመድ አወረደቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤትዋም የከተማውን ቅጥር ተጠግቶ የተሠራ ነበረና፥ እርሷም በቅጥሩ ውስጥ ተቀምጣ ነበር፤ እነርሱንም በመስኮቱ በኩል በገመድ አወረደቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ረዓብ የምትኖርበት ቤት ከከተማይቱ ቅጽር ግንብ ተጠግቶ በውስጥ በኩል የተሠራ ስለ ነበር ሰዎቹ በመስኮት በኩል ቊልቊል በተለቀቀ ገመድ ተንጠልጥለው ወደ ታች እንዲወርዱ አደረገች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤትዋም በከተማ ቅጥር የተጠጋ ነበረና፥ እርስዋም በቅጥሩ ላይ ተቀምጣ ነበረና ከመስኮቱ በገመድ አወረደቻቸው። |
ሰዎቹም፥ “ሕይወታችንን ስለ እናንተ አሳልፈን ለሞት እንሰጣለን” አሉ፤ እርስዋም አለች፥ “እግዚአብሔር ምድሪቱን በሰጣችሁ ጊዜ ቸርነትንና ጽድቅን ታደርጉልናላችሁ።” ሰዎቹም፥ “ይህን ነገራችንን ባትገልጪ እግዚአብሔር ሀገራችሁን በእውነት አሳልፎ ከሰጠን ከአንቺ ጋር ቸርነትን እናደርጋለን” አሏት።
እርስዋም፥ “የሚከተሉአችሁ እንዳያገኙአችሁ ወደ ተራራው ሂዱ፤ የሚከተሉአችሁም እስከሚመለሱ ድረስ በዚያ ሦስት ቀን ተሰውራችሁ ተቀመጡ፤ በኋላም መንገዳችሁን ትሄዳላችሁ” አለቻቸው።
ሕዝቡም ጮኹ፥ ካህናቱም ቀንደ መለከቱን ነፉ፤ ሕዝቡም የቀንደ መለከቱን ድምፅ በሰሙ ጊዜ ታላቅ ጩኸት ጮኹ፤ ቅጥሩም ወደቀ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ከተማዪቱ ገቡ፤ ሁሉም ወደ ፊታቸው ወደ ከተማዪቱ ሮጡ፤ ከተማዪቱንም እጅ አደረጉ።