ኢያሱ 19:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በባሕር በኩል በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ኢያራቆን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሜያርቆንና በኢዮጴ ፊት ለፊት ያለው ርቆን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሜያ-ርቆንን፥ በኢዮጴ ፊት ለፊት ካለው ዳርቻ ጋር ራቆንን ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሜያርቆን፥ ራቆንና እንዲሁም በኢዮጴ ዙሪያ ያለውን ግዛት ጭምር ያጠቃልላል። |
እኛም ከሊባኖስ የምትሻውን ያህል እንጨት እንቈርጣለን፤ በታንኳም አድርገን በባሕር ላይ ወደ አንተ ወደ ኢዮጴ እንልካለን፤ አንተም ወደ ኢየሩሳሌም ታስወስደዋለህ።”
ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ወደ ተርሴስ ይሸሽ ዘንድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወረደ፤ ወደ ተርሴስም የምታልፍ መርከብ አገኘ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ኰብልሎ ከእነርሱ ጋር ወደ ተርሴስ ይሄድ ዘንድ ዋጋ ሰጥቶ ወደ እርስዋ ገባ።
በኢዮጴ ሀገርም ጣቢታ የምትባል አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፤ በትርጓሜውም ዶርቃስ ይሉአታል፤ ፌቆ ማለት ነው፤ እርስዋም ብዙ ደጋግ ሥራ ትሠራ ነበር፤ ምጽዋትም ትሰጥ ነበር።
ልዳም ለኢዮጴ ቅርብ ነበርና ደቀ መዛሙርት ጴጥሮስ በዚያ እንዳለ ሰምተው ወደ እነርሱ መምጣት እንዳይዘገይ ይማልዱት ዘንድ ሁለት ሰዎችን ወደ እርሱ ላኩ።
የዳን ልጆች ነገድ ርስት በየወገኖቻቸው እነዚህ ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። የዳን ልጆችም በተራራው ላይ የሚያስጨንቋቸው አሞሬዎናውያንን አላስጨነቁአቸውም። አሞሬዎናውያንም ወደ ሸለቆዎች ይወርዱ ዘንድ አልፈቀዱላቸውም። ከእነርሱም ከርስታቸው ዳርቻ አንድ ክፍልን ወሰዱ።