ኢያሱ 19:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰባተኛው ዕጣ ለዳን ነገድ በየጐሣው ወጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰባተኛው ዕጣ ለዳን ነገድ በየወገኖቻቸው የተሰጠው የርስት ድርሻ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰባተኛውም ዕጣ ለዳን ልጆች ነገድ በየወገኖቻቸው ወጣ። |
“የነገዶችም ስም ይህ ነው። በሔትሎን መንገድ አጠገብ ወደ ሐማት መግቢያ፥ በደማስቆም ድንበር በአለው በሐጸርዔናን በሐማትም አጠገብ በሰሜን በኩል ይጀምራል። ድንበራቸውም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ይሆናል። ለዳን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆናል።
እንዲሁም ኢያሱ ምድሪቱን ሁሉ፥ ተራራማውን ሀገር፥ ደቡቡንም፥ ቆላውንም፥ ቍልቍለቱንም፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ መታ፤ ማንንም አላስቀረም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘውም ነፍስ ያለበትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም። እስከዚያም ቀን ድረስ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልደረሳቸውም ነበርና በዚያ ዘመን የዳን ነገድ የሚቀመጡባት ርስት ይሹ ነበር።