ኢያሱ 19:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ፤ የርስታቸውም ድንበር እስከ ኤሴዴቅ ጎላ ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሦስተኛው ዕጣ ለዛብሎን ነገድ በየጐሣ በየጐሣው ወጣ፤ የርስታቸውም ድንበር እስከ ሣሪድ ይደርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ፤ የርስታቸውም ድንበር እስከ ሣሪድ ደረስ ይደርስ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስተኛው ዕጣ ለዛብሎን ነገድ በየወገናቸው ወጣ፤ እነርሱም የተቀበሉት ርስት እስከ ሣሪድ ይደርሳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሦስተኛውም ዕጣ ለዛብሎን ልጆች በየወገኖቻቸው ወጣ፥ የርስታቸውም ድንበር ወደ ሣሪድ ደረሰ፥ |
የብንያምም ነገድ ዕጣ በየወገኖቻቸው በቅድሚያ ወጣ፤ የዕጣቸውም ዳርቻ በይሁዳ ልጆችና በዮሴፍ ልጆች መካከል ወጣ።
እናንተም ምድሪቱን በሰባት ክፍል ክፈሏት፤ ወደ እኔም ወዲህ አምጡልኝ፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣጥላችኋለሁ።
ድንበራቸውም በምዕራብ በኩል ወደ ማራጌላ ይወጣል፤ እስከ ቤተ ራባም ይደርሳል፤ በኢያቃንም ፊት ለፊት ወዳለው ሸለቆም ይደርሳል፤
ከይሁዳ ልጆች ክፍል የስምዖን ልጆች ርስት ሆነ፤ የይሁዳም ልጆች ዕድል ፋንታ ስለ በዛባቸው የስምዖን ልጆች በርስታቸው መካከል ወረሱ።