ኢያሱ 18:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተም ምድሪቱን በሰባት ክፍል ክፈሏት፤ ወደ እኔም ወዲህ አምጡልኝ፤ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣጥላችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰባቱን የመሬት ክፍፍል ዝርዝር መግለጫ ጽፋችሁ ወደ እኔ ታመጡና በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ እጥልላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተም ምድሩን በሰባት ክፍል ጻፉት፥ የጻፋችሁትንም ወደዚህ አምጡልኝ፤ በአምላካችንም በጌታ ፊት በዚህ ዕጣ እጥልላችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነዚህን ሰባት ክፍያዎች የሚገልጠውንም ማስረጃ በጽሑፍ አድርጋችሁ አምጡልኝ፤ አምላካችንን እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ዕጣ እጥልላችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተም ምድሩን በሰባት ክፍል ጻፉት፥ የጻፋችሁትንም ወዲህ አምጡልኝ፥ በአምላካችንም በእግዚአብሔር ፊት በዚህ ዕጣ አጣጥላችኋለሁ። |
ምድሪቱንም ትወርሳላችሁ፤ በየወገኖቻችሁም ትከፋፈሏታላችሁ፤ ለብዙዎች ድርሻቸውን አብዙላቸው፤ ለጥቂቶችም ድርሻቸውን ጥቂት አድርጉ፤ እያንዳንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደቀለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ።
ሙሴም የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፥ “እግዚአብሔር ለዘጠኙ ነገድና ለምናሴ ነገድ እኩሌታ ይሰጡአቸው ዘንድ እንደ አዘዘ በዕጣ የምትወርሱአት ምድር ይህች ናት፤
ነገር ግን የእግዚአብሔር ክህነት ርስታቸው ነውና ለሌዊ ልጆች በመካከላችሁ እድል ፋንታ የላቸውም፤ ጋድም፥ ሮቤልም፥ የምናሴም ነገድ እኩሌታ በዮርዳኖስ ማዶ በምሥራቅ በኩል የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ የሰጣቸውን ርስታቸውን ተቀብለዋል።”
ሰዎችም ተነሥተው ሄዱ፤ ኢያሱም ምድሩን ሊጽፉ የሄዱትን፥ “ሂዱ፤ ምድሩንም ዞራችሁ ጻፉት፤ ወደ እኔም ተመለሱ፤ በዚህም በሴሎ በእግዚአብሔር ፊት ዕጣ አጣጥላችኋለሁ” ብሎ አዘዛቸው።