ኢያሱ 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቤቴል ሎዛም በከሮንቲ ዳርቻ በኩል ወደ አጣሮት አውራጃ ይደርሳል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሎዛ ከምትባለው ከቤቴል ይነሣና በአጣሮት ወደሚገኘው ወደ አርካውያን ግዛት ይሻገራል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ግዛት በኩል ወደ ዓጣሮት አለፈ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቤትኤልም ተነሥቶ አርካውያን የሚኖሩበትን ዐጣሮትአዳርን በማለፍ ወደ ሎዛ ይዘልቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቤቴል ወደ ሎዛ ወጣ፥ በአርካውያንም ዳርቻ በኩል ወደ አጣሮት አለፈ፥ |
ዳዊትም ለእግዚአብሔር ወደ ሰገደበት ወደ ተራራው ራስ መጣ፤ ወዳጁ ኵሲም ልብሱን ቀደደ፤ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ።
ግዛታቸውና ማደሪያቸው ቤቴልና መንደሮችዋ፥ በምሥራቅም በኩል ነዓራን፥ በምዕራብም በኩል ጌዝርና መንደሮችዋ፥ ደግሞም ሴኬምና መንደሮችዋ፥ እስከ ጋዛና እስከ መንደሮችዋ ድረስ፤
ድንበሩም ከዚያ በደቡብ በኩል ቤቴል ወደምትባል ወደ ሎዛ ዐለፈ፤ ድንበሩም በታችኛው ቤቶሮን ደቡብ በኩል ባለው ተራራ ወደ ማአጣሮቶሬክ ወረደ።