ኢያሱ 15:60 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቴቆ፥ ኤፍራታ፥ ይኽችውም ቤተ ልሔም ናት፤ ፋጎርም፥ ኤጣንም፥ ቁሎን፥ ጠጦንም፥ ሶብሄም፥ ቃሬም፥ ጌሌም፥ ኤቴር፥ መነኮም፥ ዐሥራ አንድ ከተሞችና መንደሮቻቸው፥ ቅርያትበኣል፥ ይኽችውም የኢያርም ከተማ ናት፤ ሶቤታ፥ ሁለቱ ከተሞችና መንደሮቻቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቂርያትይዓይሪም የተባለችው ቂርያትበኣልና ረባት፤ እነዚህም ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቂርያት-ይዓሪም የምትባለው ቂርያትበኣል፥ ረባት፤ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ቂርያትባዓል ወይም ቂርያትይዓሪምና ራባ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው ያሉትን ትናንሽ ከተሞችን ይጨምራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቂርያትይዓሪም የምትባለው ቂርያትበኣል፥ ረባት፥ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
ድንበሩም ከተራራው ራስ ወደ ኔፍቶ ውኃ ምንጭ ይሄዳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ይደርሳል፤ ወደ ኢያሪም ከተማ ወደ በኣላ ይደርሳል።
ድንበሩም ወደ ባሕር ሄደ፤ በቤቶሮንም ፊት ለፊት ካለው ተራራ ወደ አዜብ ዞረ፤ መውጫውም ቂርያታርም በምትባል በይሁዳ ልጆች ከተማ በቂርያትበኣል ነበረ፤ ይህ በባሕር በኩል ነበረ።
የእስራኤልም ልጆች ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮትና ኢያሪም ነበሩ።
በቂርያትይዓሪምም ወደ ተቀመጡት ሰዎች መልእክተኞችን ልከው፥ “ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መልሰዋል፤ ወርዳችሁም ወደ እናንተ ውሰዱአት” አሉ።
የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አወጡ፤ በኮረብታውም ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አገቡአት፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።