ከራፋይም ወገን የነበረው ኤስቢ መጣ፤ የጦሩም ሚዛን ክብደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣሪያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊትንም ሊገድለው ፈለገ።
ኢያሱ 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮፎኒ ልጅ ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሱሲን፥ ተለሚንና አካሚን ከዚያ አጠፋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ዘሮች ሴሲንን፣ አኪመንንና ተላሚንን ከኬብሮን አሳደዳቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴሲንና አኪመንን ተላሚንም ከዚያ ስፍራ አሳደደ። እነዚህም የዓናቅ ትውልድ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካሌብም የዐናቅን ሦስት ልጆች ሼሻይን፥ አሒማንና ታልማይን አባረረ፤ እነርሱም የዐናቅ ዘሮች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካሌብም ሦስቱን የዔናቅን ልጆች ሴሲንና አኪመንን ተላሚንም ከዚያ አሳደደ። |
ከራፋይም ወገን የነበረው ኤስቢ መጣ፤ የጦሩም ሚዛን ክብደት ሦስት መቶ ሰቅል ናስ ነበር። አዲስ የጦር መሣሪያም ታጥቆ ነበር፤ ዳዊትንም ሊገድለው ፈለገ።
በዚያም ግዙፋን የሆኑትን አየን፤ እኛም በእነርሱ ፊት እንደ አንበጣዎች ሆን፤ እንዲሁም በፊታቸው ነበርን፤” እያሉ የሰለሉአትን ምድር ለእስራኤል ልጆች አስፈሪ አደረጓት።
አንተም የምታውቃቸው፥ ስለ እነርሱም፦ በዔናቅ ልጆች ፊት መቆም ማን ይችላል? ሲባል የሰማኸው ታላቅ፥ ብዙና ረዥም ሕዝብ የዔናቅ ልጆች ናቸው።
በዚያ ጊዜም ኢያሱ ሄደ፤ በተራራማውም ሀገር የሚኖሩ ኤናቃውያንን ከኬብሮንና ከዳቤር፥ ከአናቦትም፥ ከእስራኤልም ተራራ ሁሉ፥ ከይሁዳም ተራራ ሁሉ አጠፋቸው፤ ኢያሱም ከከተሞቻቸው ጋር ፈጽሞ አጠፋቸው።
ይሁዳም በኬብሮን ወደሚኖሩ ከነዓናውያን ሄደ። የኬብሮንም ሰዎች ወጥተው ተቀበሉት፤ የኬብሮንም ስም አስቀድሞ ቂርያታርቦቅሴፌር ነበረ። የኤናቅንም ትውልድ ሴሲንና አኪማምን፥ ተለሜንንም ገደሉአቸው።
ሙሴም እንደ ተናገረ ለካሌብ ኬብሮንን ሰጡት፤ ከዚያም ሠላሳ ከተሞችን ወረሰ፤ ከዚያም ሦስቱን የዔናቅ ልጆች አስወገዳቸው።