ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
ኢያሱ 11:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አገልጋዩን ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ ሙሴ ኢያሱን አዝዞት ነበር፤ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔርም ሙሴን ካዘዘው ሁሉ ምንም አላስቀረም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘው ሁሉ፣ ሙሴም ኢያሱን አዘዘው፤ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ካዘዘው ሁሉ እርሱ ያልፈጸመው አንዳች ነገር አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ባርያውን ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ሙሴ ኢያሱን አዝዞት ነበር፥ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ፤ ጌታ ሙሴን ካዘዘው ሁሉ ምንም አላስቀረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ትእዛዙን ለአገልጋዩ ለሙሴ ሰጠ፤ ሙሴም ለኢያሱ ሰጠ፤ ኢያሱም ትእዛዞችን ፈጸመ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ኢያሱ ሁሉን ነገር አደረገ፤ አንዳችም አላስቀረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘው እንዲሁ ሙሴ ኢያሱን አዝዞት ነበር፥ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ፥ እግዚአብሔር ሙሴን ካዘዘው ሁሉ ምንም አላስቀረም። |
ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
በዚያችም ምድር የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ አጥፉአቸው፤ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፤ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፤ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! ከአዝሙድና ከእንስላል ከከሙንም አሥራት ስለምታወጡ፥ ፍርድንና ምሕረትን ታማኝነትንም፥ በሕግ ያለውን ዋና ነገር ስለምትተዉ፥ ወዮላችሁ፤ ሌላውን ሳትተዉ ይህን ልታደርጉ ይገባችሁ ነበር።
የእንስላልና የጤና አዳም፥ ከአትክልትም ሁሉ ዐስራት የምታገቡ ፍርድንና የእግዚአብሔርን ፍቅር ቸል የምትሉ እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! ይህንም ልታደርጉ ይገባችኋል፥ ያንም አትተዉ።
አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ በፊትህ ያልፋል፤ እርሱ እነዚህን አሕዛብ ከፊትህ ያጠፋቸዋል፤ ትወርሳቸውማለህ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ ኢያሱ በፊትህ ይሄዳል።
ሙሴም ኢያሱን ጠርቶ በእስራኤል ሁሉ ፊት፦ ‘አንተ ከዚህ ሕዝብ ጋር እግዚአብሔር ለአባቶቻቸው እንዲሰጥ ወደ ማለላቸው ምድር ትገባለህና፥ እርስዋንም ለእነርሱ ታወርሳለህና ጽና፤ በርታ።
ዛሬ እኔ ያዘዝኋችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትጠብቃላችሁ እንጂ ባዘዝኋችሁ ቃል ላይ አትጨምሩም፤ ከእርሱም አታጐድሉም።
እነሆ፥ እናንተ ገብታችሁ በምትወርሱአት ምድር ውስጥ እንዲህ ታደርጉ ዘንድ አምላኬ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ ሥርዐትና ፍርድን አሳየኋችሁ።
አምላክህ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና በመታሃቸው ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፤ አትማራቸውም፤
አገልጋዬ ሙሴ እንደ አዘዘህ ሕግን ሁሉ ትጠብቅና ታደርግ ዘንድ ጽና፤ እጅግም በርታ፤ ሁሉን እንዴት እንደምትሠራ ታውቅ ዘንድ ከእርሱ ወደ ቀኝ ወደ ግራም አትበል።
የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን መንግሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ ያዘ፤ በሰይፍም መታቸው፤ ፈጽሞም አጠፋቸው።
የእስራኤልም ልጆች የእነዚህን ከተሞች ምርኮ ሁሉ፥ ከብቶቹንም ለራሳቸው ዘረፉ፤ ሰዎቹን ሁሉ ግን እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍ ስለት መቱአቸው፤ እስትንፋስ ያለውንም ሁሉ አንድም አላስቀሩም።
ኢያሱም ያን ምድር ሁሉ፥ ተራራማውን፥ ደቡቡንም ሁሉ፥ የጎሶምንም ምድር ሁሉ ፥ ሜዳውንም፥ በምዕራብ በኩል ያለውንም፥ የእስራኤልንም ተራራማውንና ቆላውን ያዘ፤
“ሳኦል እኔን ከመከተል ተመልሶአልና፥ ትእዛዜንም አልፈጸመምና ስላነገሥሁት ተጸጸትሁ።” ሳሙኤልም አዘነ። ሌሊቱንም ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።