ኢዩም ከአክአብ ቤት በኢይዝራኤል የቀረውን ሁሉ፥ ታላላቆቹንም ሁሉ፥ ወዳጆቹንና ካህናቱን ሁሉ ገደላቸው፤ ከእነርሱ አንድስ እንኳ አላስቀረም።
ኢያሱ 10:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እርስዋንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠ፤ እርስዋንም በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መታ፤ በእርስዋም አንዱን ስንኳ አላስቀረም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረገው በልብና ንጉሥ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም እግዚአብሔር ከተማዪቱንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጣቸው። ኢያሱ ከተማዪቱንና በውስጧ ያለውን ሁሉ በሰይፍ ስለት አጠፋ፤ አንድም ሰው አላስተረፈም። በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ ያደረገውንም በልብና ንጉሥ ላይ ደገመው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እርሷንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠ፤ እርሷንም በእርሷም ያሉትን ሰዎች ሁሉ በሰይፍ ስለት መታ፥ በእርሷም አንድም እንኳ አላስቀረም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ ላይ እንዳደረገው እንዲሁ በልብና ንጉሥ ላይ አደረገ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም በርስዋና በንጉሥዋ በእስራኤል ላይ ለእስራኤላውያን ድልን ሰጣቸው፤ ኢያሱም ከተማይቱንና በእርስዋ ያሉትን ሰዎች አጠፋ፤ በንጉሥዋም ላይ በኢያሪኮ ንጉሥ ላይ እንዳደረገው አደረገበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እርስዋንና ንጉሥዋን በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ እርስዋንም በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ በሰይፍ ስለት መታ፥ በእርስዋም አንዱን ስንኳ አላስቀረም፥ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረገው በልብና ንጉሥ አደረገ። |
ኢዩም ከአክአብ ቤት በኢይዝራኤል የቀረውን ሁሉ፥ ታላላቆቹንም ሁሉ፥ ወዳጆቹንና ካህናቱን ሁሉ ገደላቸው፤ ከእነርሱ አንድስ እንኳ አላስቀረም።
ምድሪቱም በእግዚአብሔር ፊት ድል እስክትሆን ድረስ ከዚያም በኋላ ትመለሳላችሁ፤ በእግዚአብሔርም ፊት በእስራኤል ዘንድ ንጹሓን ትሆናላችሁ፤ ይህች ምድርም በእግዚአብሔር ፊት ርስት ትሆናችኋለች።
አምላክህ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ በሰጣቸውና በመታሃቸው ጊዜ፥ ፈጽመህ አጥፋቸው፤ ከእነርሱም ጋር ቃል ኪዳን አታድርግ፤ አትማራቸውም፤
በዚያም ቀን መቄዳን ያዟት፤ እርስዋንና ንጉሥዋንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፤ በእርስዋም ያሉትን ነፍሳት ሁሉ ፈጽመው አጠፉአቸው፤ ከእነርሱም አንዱን ስንኳ አላስቀሩም፤ የዳነም፥ ያመለጠም የለም፤ በኢያሪኮም ንጉሥ እንዳደረጉ በመቄዳ ንጉሥ አደረጉ።
የእግዚአብሔርም አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው፥ ኢያሱ የእነዚህን መንግሥታት ከተሞች ሁሉ፥ ንጉሦቻቸውንም ሁሉ ያዘ፤ በሰይፍም መታቸው፤ ፈጽሞም አጠፋቸው።
የእስራኤልም ልጆች ተከትለዋቸው በነበረበት በተራራው ቍልቍለትና በምድረ በዳ የጋይን ሰዎች መግደልን ከጨረሱ፥ ሁሉንም በጦር ወግተው ከአጠፉአቸው በኋላ ኢያሱ ወዲያውኑ ወደ ጋይ ተመልሶ፥ በሰይፍ አጠፋት።
የጋይንም ንጉሥ በዝግባ ዛፍ ላይ ሰቀለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ ያወርዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛፉም አወረዱት፤ በከተማዪቱም በር አደባባይ ጣሉት፤ በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት።