ሣራም በቈላ ውስጥ ባለች አርባቅ በምትባል ከተማ ሞተች፤ እርስዋም በከነዓን ምድር ያለች ኬብሮን ናት፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና ሊያለቅስላት ተነሣ።
ኢያሱ 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒቤዜቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ሆሃም ወደተባለው የኬብሮን ንጉሥ ጲርአም ወደተባለው የያርሙት ንጉሥ፣ ያፊዓ ወደተባለው የለኪሶ ንጉሥና ዳቤር ወደተባለው የዔግሎን ንጉሥ በመላክ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ጲርአም፥ ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ ዔግሎም ንጉሥም ወደ ዳቤር እንዲህ ብሎ ላከ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የኢየሩሳሌሙ ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ሆሃም ተብሎ ለሚጠራው ለኬብሮን ንጉሥ፥ ፒራም ለተባለው ለያርሙት ንጉሥ፥ ያፊዓ ለተባለው ለላኪሽ ንጉሥና ደቢር ለተባለው ለዔግሎን ንጉሥ እንዲህ የሚል መልእክት ላከ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ሆሃም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ጲርአም፥ ወደ ለኪሶ ንጉሥም ወደ ያፊዓ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፦ ወደ እኔ ውጡ፥ |
ሣራም በቈላ ውስጥ ባለች አርባቅ በምትባል ከተማ ሞተች፤ እርስዋም በከነዓን ምድር ያለች ኬብሮን ናት፤ አብርሃምም ለሣራ ሊያዝንላትና ሊያለቅስላት ተነሣ።
እርሱም፥ “ሄደህ ወንድሞችህና በጎቹ ደኅና እንደ ሆኑ እይ፤ ወሬአቸውንም አምጣልኝ” አለው። ወደ ኬብሮንም ቆላ ላከው፤ ወደ ሴኬምም መጣ።
የይሁዳም ንጉሥ ሕዝቅያስ፥ “በድያለሁ፥ ከእኔ ተመለስ፤ የምትጭንብኝንም ሁሉ እሸከማለሁ” ብሎ ወደ አሦር ንጉሥ ወደ ለኪሶ መልእክተኞችን ላከ። የአሦርም ንጉሥ በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ላይ ሦስት መቶ መክሊት ብርና ሠላሳ መክሊት ወርቅ ጫነበት።
የአሦርም ንጉሥ ተርታንንና ራፌስን ራፋስቂስንም ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላካቸው። ወጥተውም ወደ ኢየሩሳሌም ደረሱ፤ በአጣቢውም እርሻ መንገድ ባለችው በላዪኛዪቱ ኩሬ መስኖ አጠገብ ቆሙ።
የባቢሎንም ንጉሥ ሠራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳን ከተሞች ሁሉ፥ ለኪሶንና አዚቃንም ይወጋ ነበር። እነዚህ የተመሸጉ ከተሞች በይሁዳ ከተሞች መካከል ቀርተው ነበርና።
በለኪሶ የምትቀመጪ ሆይ፥ ሰረገላውን ለፈረስ እሰሪ፥ እርስዋ ለጽዮን ሴት ልጆች የኃጢአት መጀመሪያ ነበረች፥ የእስራኤል በደል በአንቺ ዘንድ ተገኝቶአልና።
ወደ ምድረ በዳም ወጡ፤ ወደ ኬብሮንም ደረሱ፤ በዚያም የዔናቅ ዘሮች አኪማን፥ ሴሲ፥ ተላሚ ነበሩ። ኬብሮንም በግብፅ ካለችው ከጣኔዎስ ከተማ በፊት ሰባት ዓመታት ተሠርታ ነበር።
እንዲህም ሆነ፤ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒቤዜቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ፥ ፈጽሞም እንዳጠፋት፥ በኢያሪኮና በንጉሥዋም ያደረገውን እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋም እንዳደረገ፥ የገባዖንም ሰዎች ከኢያሱና ከእስራኤል ጋር ሰላም እንዳደረጉ፥ በመካከላቸውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥
እንዲህም አደረጉ፤ አምስቱንም ነገሥት፥ የኢየሩሳሌምን ንጉሥ፥ የኬብሮንንም ንጉሥ፥ የየርሙትንም ንጉሥ፥ የላኪስንም ንጉሥ፥ የአዶላምንም ንጉሥ ከዋሻው ወደ እርሱ አወጡአቸው።
አምስቱም የኢያቡሴዎን ነገሥት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የላኪስ ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፤ ከገባዖንም ጋር ሊጋጠሙ ከበቡአት።
የኬብሮንም ስም አስቀድሞ የአርቦቅ ከተማ ትባል ነበር፤ እርስዋም የዔናቃውያን ዋና ከተማ ነበረች። ምድሪቱም ከውጊያ ዐረፈች።
በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሴዎናውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልተቻላቸውም፤ ኢያቡሴዎናውያንም እስከ ዛሬ ድረስ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።
ኢየሩሳሌም የምትባል የኢያቡሴዎን ከተማና የኢያሪሞን ከተማ ገባዖን፤ ዐሥራ ሦስት ከተሞችና መንደሮቻቸው። የብንያም ልጆች ርስት በየወገኖቻቸው ይህ ነበረ።