Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢያሱ 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 “ወደ እኔ ኑ፤ ከኢ​ያ​ሱና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ጋር ሰላም አድ​ር​ገ​ዋ​ልና ገባ​ዖ​ንን ለመ​ው​ጋት አግ​ዙኝ” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “ወደዚህ ወጥታችሁ አግዙኝ፤ ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋራ ሰላምን መሥርታለችና ገባዖንን እንምታ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 “ወደ እኔ ውጡ፥ ከኢያሱና ከእስራኤልም ልጆች ጋር የሰላም ስምምነት አድርገዋልና ገባዖንን ለመምታት አግዙኝ።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “ገባዖን ከኢያሱና ከእስራኤላውያን ጋር በሰላም አብሮ የመኖር ስምምነት ስላደረገች እርስዋን ለመውጋት መጥታችሁ እርዱኝ፤”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከኢያሱና ከእስራኤልም ልጆች ጋር ሰላም አድርገዋልና ገባዖንን ለመምታት አግዙኝ አለ።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 10:4
15 Referencias Cruzadas  

ኢያ​ሱም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሰላም አደ​ረገ፤ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ተ​ዋ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ማሉ​ላ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ አዶ​ኒ​ቤ​ዜቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ፥ ፈጽ​ሞም እን​ዳ​ጠ​ፋት፥ በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም ያደ​ረ​ገ​ውን እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረገ፥ የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ከኢ​ያ​ሱና ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ሰላም እን​ዳ​ደ​ረጉ፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥


ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።


በዚህም ነገር ወደዚያ መዳራት ብዛት ከእነርሱ ጋር ስለማትሮጡ እየተሳደቡ ይደነቃሉ፤


አመንዝሮች ሆይ! ዓለምን መውደድ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል።


በእውነትም በክርስቶስ ኢየሱስ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ሊኖሩ የሚወዱ ሁሉ ይሰደዳሉ።


እየ​ጮ​ሁም እን​ዲህ አሉ፥ “እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሆይ፥ ርዱን፤ በየ​ስ​ፍ​ራው ሕዝ​ባ​ች​ንን፥ ኦሪ​ት​ንም፥ ይህ​ንም ስፍራ የሚ​ቃ​ወም ትም​ህ​ርት ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር እነሆ፥ ይህ ሰው ነው፤ አሁ​ንም አረ​ማ​ው​ያ​ንን ወደ መቅ​ደስ አስ​ገባ፤ ቤተ መቅ​ደ​ስ​ንም አረ​ከሰ።


እና​ን​ተስ ከዓ​ለም ብት​ሆኑ ዓለም በወ​ደ​ዳ​ችሁ ነበር፤ ዓለም ወገ​ኖ​ቹን ይወ​ዳ​ልና፤ ነገር ግን እኔ ከዓ​ለም መረ​ጥ​ኋ​ችሁ እንጂ እና​ንተ ከዓ​ለም አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምና ስለ​ዚህ ዓለም ይጠ​ላ​ች​ኋል።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ “እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።


አም​ስ​ቱም የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን ነገ​ሥት፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ የኬ​ብ​ሮን ንጉሥ፥ የየ​ር​ሙት ንጉሥ፥ የላ​ኪስ ንጉሥ፥ የአ​ዶ​ላም ንጉሥ፥ ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ጋር ተሰ​ብ​ስ​በው ወጡ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ጋር ሊጋ​ጠሙ ከበ​ቡ​አት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios