ዮናስ 3:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ተነሥተህ ወደዚያች ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የነገርሁህንም የመጀመሪያውን ስብከት ስበክላት” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሄደህ የምነግርህን መልእክት ስበክላት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ተነሥ፥ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፥ እኔ የምነግርህን መልዕክት አውጅ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ተነሥተህ ወደ ታላቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ እኔም የምነግርህን ቃል ለሕዝቡ ዐውጅ።” |
አንተ ግን ወገብህን ታጠቅ፤ ተነሥም፤ ያዘዝሁህንም ሁሉ ንገራቸው፤ ከፊታቸውም የተነሣ አትፍራ። በፊታቸውም አትደንግጥ አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር ግን እንዲህ አለኝ፥ “ወደምልክህ ሁሉ ዘንድ ትሄዳለህና፥ የማዝዝህንም ሁሉ ትናገራለህና፦ ሕፃን ነኝ አትበል።
ዮናስም ተነሥቶ እንደ እግዚአብሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም ታላቅ ከተማ ነበረች፤ የቅጥርዋም ዙሪያ በእግር የሦስት ቀን መንገድ ያህል ነበረ።
ከዚህም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ያን የዳነውን ሰው በቤተ መቅደስ አገኘውና፥ “እነሆ፥ ድነሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል ተጠንቀቅ” አለው።