Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮናስ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዮና​ስም ተነ​ሥቶ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነ​ዌም ታላቅ ከተማ ነበ​ረች፤ የቅ​ጥ​ር​ዋም ዙሪያ በእ​ግር የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ያህል ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዮናስም የእግዚአብሔርን ቃል ታዘዘ፤ ወደ ነነዌም ሄደ። በዚህ ጊዜ ነነዌ ታላቅ ከተማ ነበረች፤ እርሷንም ከዳር እስከ ዳር ለመጐብኘት ሦስት ቀን ያስፈልግ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዮናስም ተነሣና ጌታ እንደ ተናገረው ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌም እጅግ ታላቅ ከተማ ነበረች፥ ለማቋረጥም ሦስት ቀን ይፈጅ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዮናስም ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ተነሥቶ ወደ ነነዌ ሄደ፤ ነነዌ እጅግ ታላቅ ከተማ ከመሆንዋ የተነሣ ከተማዋን በመላ ለማዳረስ ሦስት ቀን ይፈጅ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ዮናስ 3:3
9 Referencias Cruzadas  

አብ​ር​ሃ​ምም በማ​ለዳ ተነ​ሥቶ አህ​ያ​ውን ጫነ፤ ሁለ​ቱ​ንም ሎሌ​ዎ​ቹ​ንና ልጁን ይስ​ሐ​ቅን ከእ​ርሱ ጋር ወሰደ፤ ዕን​ጨ​ት​ንም ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ሰነ​ጠቀ፤ ተነ​ሥ​ቶም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዳ​ለው ቦታ ሄደ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ደረሰ።


ራሔ​ልም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ አደ​ረ​ገኝ፤ ብርቱ ትግ​ል​ንም ከእ​ኅቴ ጋር ታገ​ልሁ፤ አሸ​ነ​ፍ​ሁም፤ እኅ​ቴ​ንም መሰ​ል​ኋት” አለች፤ ስሙ​ንም ንፍ​ታ​ሌም ብላ ጠራ​ችው።


ጽድ​ቅ​ህን እንደ ብር​ሃን፥ ፍር​ድ​ህ​ንም እንደ ቀትር ያመ​ጣ​ታል።


ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሁህ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ነኝና፤ አፍ​ህን አስፋ፥ እሞ​ላ​ዋ​ለ​ሁም።


የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ሰና​ክ​ሬም ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ተመ​ል​ሶም በነ​ነዌ ተቀ​መጠ።


“ተነ​ሥ​ተህ ወደ ታላ​ቂቱ ከተማ ወደ ነነዌ ሂድ፤ የክ​ፋ​ታ​ቸ​ውም ጩኸት ወደ ፊቴ ወጥ​ቶ​አ​ልና ለእ​ነ​ርሱ ስበክ።”


እኔስ ቀኛ​ቸ​ው​ንና ግራ​ቸ​ውን የማ​ይ​ለዩ ከመቶ ሃያ ሺህ የሚ​በ​ልጡ ሰዎ​ችና ብዙ እን​ስ​ሶች ላሉ​ባት ለታ​ላ​ቂቱ ከተማ ለነ​ነዌ አላ​ዝ​ን​ምን?” አለው።


ሉቃስ ብቻ ከእኔ ጋር አለ፤ ማርቆስ ለአገልግሎት ብዙ ይጠቅመኛልና ይዘኸው ከአንተ ጋር አምጣው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos