ዮሐንስ 9:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈሪሳውያንም አንዳንዶች፥ “ይህ ሰው ከእግዚአብሔር አይደለም፤ ሰንበትን አያከብርምና” አሉ፤ ሌሎች ግን “ኀጢኣተኛ ሰው እንዲህ ያለ ተአምራት ማድረግ እንዴት ይችላል?” አሉ፤ እርስ በርሳቸውም ተለያዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ፣ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር፣ ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን፣ “ኀጢአተኛ፣ እንዲህ ያሉትን ታምራዊ ምልክቶች እንዴት ሊያደርግ ይችላል?” አሉ። በመካከላቸውም አለመስማማት ተፈጠረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ “ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርምና ከእግዚአብሔር አይደለም፤” አሉ። ሌሎች ግን “ኃጢአትኛ ሰው እንደነዚህ ያሉ ምልክቶችን ሊያደርግ እንዴት ይችላል?” አሉ። በመካከላቸውም መለያየት ሆነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ፥ “ይህ ሰው ሰንበትን ስለማያከብር ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን “ታዲያ፥ ኃጢአተኛ የሆነ ሰው እነዚህን ተአምራት እንዴት ማድረግ ይችላል?” አሉ። በዚህ ምክንያት በመካከላቸው መለያየት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ፦ “ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርምና ከእግዚአብሔር አይደለም” አሉ። ሌሎች ግን፦ “ኃጢአትኛ ሰው እንደነዚህ ያሉ ምልክቶች ሊያደርግ እንዴት ይችላል?” አሉ። |
የምኵራቡ ሹምም ጌታ ኢየሱስ በሰንበት ፈውሶአልና፤ እየተቈጣ መልሶ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፥ “ሥራችሁን የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች ያሉ አይደለምን? ያንጊዜ ኑና ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም።”
ሌላ ያልሠራውን ሥራ በመካከላቸው ባልሠራ ኖሮ ኀጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተዋል፤ ጠልተውማል።
ጌታችን ኢየሱስም በቃና ዘገሊላ ያደረገው የተአምራት መጀመሪያ ይህ ነው፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም አመኑበት።
እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ መጥቶ እንዲህ አለው፥ “መምህር ሆይ፥ ልታስተምር ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርገውን ይህን ተአምር ሊያደርግ የሚችል የለምና።”
እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክርነት የሚበልጥ ምስክር አለኝ፤ ልሠራውና ልፈጽመው አባቴ የሰጠኝ ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ያ የምሠራው ሥራ ምስክሬ ነውና።
የሙሴ ሕግ እንዳይሻር ሰው በሰንበት የሚገዘር ከሆነ እንግዲያ ሰውን ሁለንተናውን በሰንበት ባድነው ለምን ትነቅፉኛላችሁ?
ዕውር የነበረውንም ሰው ዳግመኛ ጠርተው፥ “ሂድ ለእግዚአብሔር ምስጋና አቅርብ፤ ይህ ሰው ኀጢኣተኛ እንደ ሆነ እኛ እናውቃለን” አሉት።