እርስዋም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? አንተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።
ዮሐንስ 8:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ኅሊናቸው ወቅሶአቸው ከሽማግሌዎች ጀምሮ እስከ ኋለኞቹ ድረስ፥ አንዳንድ እያሉ ወጡ፤ ጌታችን ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴትዮዪቱም በመካከል ቆማ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን እንደ ሰሙ፣ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ በአንድ ወጡ፤ ሴትዮዋም እዚያው ፊቱ እንደ ቆመች ኢየሱስ ብቻውን ቀረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ይህን ሲሰሙ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ ከሽማግሌዎች ጀምሮ ሁሉም አንድ በአንድ ከዚያ ሄዱ፤ ስለዚህ ኢየሱስ በመካከል ቆማ ከነበረችው ሴት ጋር ብቻውን ቀረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸዋና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። |
እርስዋም ኤልያስን፥ “የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ እኔ ከአንተ ጋር ምን አለኝ? አንተስ ከእኔ ጋር ምን አለህ? ኀጢአቴንስ ታሳስብ ዘንድ፥ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን?” አለችው።
ንጉሡም ደግሞ ሳሚን፥ “አንተ በአባቴ በዳዊት ላይ የሠራኸውን፥ ልብህም ያሰበውን ክፋት ሁሉ ታውቃለህ፤ እግዚአብሔርም ክፋትህን በራስህ ላይ ይመልሳል።
ይህንም ባለ ጊዜ በእርሱ ላይ በጠላትነት የተነሡበት ሁሉ አፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከእርሱ ስለሚደረገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላቸው።
ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ፥ “የዓለም ብርሃን እኔ ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃንን ያገኛል እንጂ በጨለማ ውስጥ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው።
በጥዋትም ገስግሦ ዳግመኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ እርሱም ተቀምጦ ያስተምራቸው ጀመር።
በልባቸው የተጻፈውን የሕግ ሥራ ያሳያሉ፤ ከሥራቸውም የተነሣ ይታወቃል፤ ሕሊናቸውም ይመሰክርባቸዋል፤ ይፈርድባቸዋልም።
አታመንዝሩ ትላለህ፤ ነገር ግን አንተ ራስህ ታመነዝራለህ፤ ወደ ጐልማሳ ሚስትም ትሄዳለህ፤ ጣዖትን ትጸየፋለህ፤ አንተ ግን ቤተ መቅደስን ትዘርፋለህ።