ዮሐንስ 7:51 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ፤ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሕጋችን፣ አስቀድሞ አንድን ሰው ሳይሰማና ምን እንዳደረገ ሳይረዳ ይፈርድበታልን?” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ፥ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በሕጋችን መሠረት አንድ ሰው የክስ መልስ አስቀድሞ ሳይሰማለትና ምን እንዳደረገ ሳይታወቅ ይፈረድበታልን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) “ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ማንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” አላቸው። |
ጳውሎስም መልሶ፥ “አንተ የተለሰነ ግድግዳ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዝዛለህን? እግዚአብሔር በቍጣው መቅሠፍት ይመታሃል” አለው።
በፍርድም ፊት አትዩ፤ ለትልቁም፥ ለትንሹም በእውነት ፍረዱ፤ ለሰው ፊት አታድሉ፤ ፍርድ የእግዚአብሔር ነውና። አንድ ነገር ቢከብዳችሁ እርሱን ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም እሰማዋለሁ፤