ዮሐንስ 7:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈሪሳውያንም ሕዝቡ በእርሱ ምክንያት እንደ አጕረመረሙ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ይይዙት ዘንድ ሎሌዎቻቸውን ላኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈሪሳውያን፣ ሕዝቡ ስለ እርሱ በጕምጕምታ የሚነጋገረውን ነገር ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም እንዲይዙት የቤተ መቅደስ ጠባቂዎችን ላኳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈሪሳውያን ሕዝቡ ስለ እርሱ እንደዚህ ሲያንጐራጉሩ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሊይዙት ዘቦችን ላኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎቹ ስለ ኢየሱስ በሹክሹክታ ሲነጋገሩ ፈሪሳውያን ሰሙ፤ ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ኢየሱስን ለማስያዝ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎችን ላኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈሪሳውያን ሕዝቡ ሰለ እርሱ እንደዚህ ሲያንጐራጕሩ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችም ፈሪሳውያም ሊይዙት ሎሌዎችን ላኩ። |
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
ፈሪሳውያንም እርስ በርሳቸው፥ “የምታገኙት ምንም ጥቅም እንደሌለ ታያላችሁን? እነሆ፥ ዓለም ሁሉ ተከትሎታል” ተባባሉ።
ይሁዳም ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን ወታደሮችን ተቀበለ፤ ሎሌዎቻቸውንም በረዳትነት ወሰደ፤ ፋኖስና የችቦ መብራት፥ የጦር መሣሪያም ይዞ ወደዚያ ሄደ።
ከዚህም በኋላ የቤተ መቅደሱ ሹም ከሎሌዎቹ ጋር ሔዶ አባብሎ አመጣቸው፤ በግድም አይደለም፤ በድንጋይ እንዳይደበድቧቸው ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።
ሳኦልም ዳዊትን ያመጡት ዘንድ መልእክተኞችን ላከ፤ የነቢያትንም ጉባኤ አገኙ፤ ሳሙኤልም አለቃቸው ሆኖ በመካከላቸው ቆሞ ነበረ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በሳኦል መልእክተኞች ላይ ወረደ፤ እነርሱም ትንቢት ይናገሩ ጀመር።