ዮሐንስ 5:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለአብ በራሱ ሕይወት እንዳለው፥ እንዲሁም ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው ሁሉ፣ ወልድም በራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብ በእራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በእራሱ ሕይወት እንዲኖረው ሰጥቶታልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብ ራሱ የሕይወት ምንጭ እንዲሆን አድርጎታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብ በራሱ ሕይወት እንዳለው እንዲሁ ደግሞ ለወልድ በራሱ ሕይወት እንዲሆረው ሰጥቶታልና። |
እግዚአብሔርም ለሙሴ ነገረው፤ እንዲህ ሲል፥ “ያለና የሚኖር እኔ ነኝ፤ እንዲህ ለእስራኤል ‘ያለና የሚኖር’ ወደ እናንተ ላከኝ ትላቸዋለህ” አለው።
እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም።
ከእኔ ማንም አይወስዳትም፤ ነገር ግን እኔ በፈቃዴ እሰጣታለሁ፤ እኔ ላኖራት ሥልጣን አለኝ፤ መልሼ እወስዳት ዘንድ ሥልጣን አለኝና፤ ይህንም ትእዛዝ ከአባቴ ተቀበልሁ።”
ገና ጥቂት ጊዜ አለ፤ እንግዲህ ወዲህም ዓለም አያየኝም፤ እናንተ ግን ታዩኛላችሁ፤ እኔ ሕያው ነኝና፤ እናንተም ሕያዋን ትሆናላችሁ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ውኃ አጠጪኝ ብሎ የሚለምንሽ ማን እንደ ሆነ ብታውቂስ አንቺ ደግሞ በለመንሺው ነበር፤ እርሱም የሕይወትን ውኃ በሰጠሽ ነበር” ብሎ መለሰላት።
እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን፥ ሌላውንም ነገር ሁሉ ለሁሉ ይሰጣልና እንደ ችግረኛ የሰው እጅ አያገለግለውም።
መጽሐፍ እንዲሁ ብሎአልና የመጀመሪያው ሰው አዳም በነፍስ ሕያው ሆኖ ተፈጠረ፤ ሁለተኛው አዳም ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው።
እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።
በዙፋኑ መካከል ያለው በጉ እረኛቸው ይሆናልና፤ ወደ ሕይወትም ውሃ ምንጭ ይመራቸዋልና፤ እግዚአብሔርም እንባዎችን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል።”