በብላቴናውም ላይ ሦስት ጊዜ እፍ አለበት፤ ወደ እግዚአብሔርም፥ “አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመለስ ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ እግዚአብሔርን ጠራው።
ዮሐንስ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብ ሙታንን እንደሚያስነሣቸው፥ ሕይወትንም እንደሚሰጣቸው እንዲሁ ወልድም ለሚወድዳቸው ሕይወትን ይሰጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም አብ ሙታንን እንደሚያስነሣ፣ ሕይወትንም እንደሚሰጥ፣ ወልድም ደግሞ ለሚፈቅደው ሁሉ ሕይወትን ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብ ሙታንን እንደሚያስነሣቸው፥ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብ የሞቱትን እንደሚያስነሣና ሕይወትን እንደሚሰጣቸው፥ ወልድም እንዲሁ ለፈለገው ሰው ሕይወትን ይሰጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብ ሙታንን ይንደሚያነሣ ሕይወትም እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣቸዋል። |
በብላቴናውም ላይ ሦስት ጊዜ እፍ አለበት፤ ወደ እግዚአብሔርም፥ “አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመለስ ዘንድ እለምንሃለሁ” ብሎ እግዚአብሔርን ጠራው።
የእስራኤልም ንጉሥ ደብዳቤውን ባነበበ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ፥ “ሰውን ከለምጹ እፈውስ ዘንድ ይህ ሰው ወደ እኔ መስደዱ እኔ በውኑ ለመግደልና ለማዳን የምችል አምላክ ነኝን? ተመልከቱ፥ የጠብ ምክንያት እንደሚፈልግብኝ ተመልከቱ” አለ።
ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው፤ ሥጋ ግን አንዳች አይጠቅምም፤ ይህም እኔ የምነግራችሁ ቃል መንፈስ ነው፤ ሕይወትም ነው።
ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ለይቶ ያስነሣው የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረባችሁ ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን ለይቶ ያስነሣው እርሱ አድሮባችሁ ባለ መንፈሱ ለሟች ሰውነታችሁ ሕይወትን ይሰጣታል።
መጽሐፍ እንዲሁ ብሎአልና የመጀመሪያው ሰው አዳም በነፍስ ሕያው ሆኖ ተፈጠረ፤ ሁለተኛው አዳም ግን ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ነው።
እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ ዕወቁ፤ ዕወቁ። እኔ እገድላለሁ፤ አድንማለሁ፤ እኔ እገርፋለሁ፤ ይቅርም እላለሁ፤ ከእጄም የሚያመልጥ የለም።