Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 5:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና የሚ​ሠ​ራ​ው​ንም ሥራ ሁሉ ያሳ​የ​ዋል፤ እና​ን​ተም ታደ​ንቁ ዘንድ ከዚህ የሚ​በ​ልጥ ሥራን ያሳ​የ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 አብ ወልድን ስለሚወድድ የሚያደርገውን ሁሉ ያሳየዋል፤ ትደነቁም ዘንድ ከእነዚህም የሚበልጥ ነገር ያሳየዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አብ ወልድን ይወዳልና፤ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 አብ ወልድን ስለሚወድ የሚሠራውን ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም እንድትደነቁ ከዚህ የበለጠ ሥራም ያሳየዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 አብ ወልድን ይወዳልና፥ የሚያደርገውንም ሁሉ ያሳየዋል፤ እናንተም ትደነቁ ዘንድ ከዚህ የሚበልጥ ሥራ ያሳየዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 5:20
17 Referencias Cruzadas  

አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና፥ ሁሉን በእጁ ሰጠው።


እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” አለ።


ከገናናው ክብር “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤” የሚል ያ ድምፅ በመጣለት ጊዜ ከእግዚአብሔር አብ ክብርንና ምስጋናን ተቀብሎአልና፤


እኔን የወ​ደ​ድ​ህ​በት ፍቅር በእ​ነ​ርሱ ይኖር ዘንድ፥ እኔም በእ​ነ​ርሱ እኖር ዘንድ ስም​ህን ነገ​ር​ኋ​ቸው፤ ደግ​ሞም እነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤”


እን​ግ​ዲህ ወዲህ ባሮች አል​ላ​ች​ሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አያ​ው​ቅ​ምና፤ እና​ን​ተን ግን ወዳ​ጆች እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በአ​ባቴ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ሁሉ ነግ​ሬ​አ​ች​ኋ​ለ​ሁና።


“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በእኔ የሚ​ያ​ምን እኔ የም​ሠ​ራ​ውን ሥራ እር​ሱም ይሠ​ራል፤ ከዚ​ያም የሚ​በ​ልጥ ይሠ​ራል፤ እኔ ወደ አብ እሄ​ዳ​ለ​ሁና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከአ​ባቴ ብዙ መል​ካም ሥራ አሳ​የ​ኋ​ችሁ፤ ከእ​ነ​ርሱ በየ​ት​ኛው ሥራ ምክ​ን​ያት ትወ​ግ​ሩ​ኛ​ላ​ችሁ?”


መል​ካም የሠሩ ለሕ​ይ​ወት ትን​ሣኤ፥ ክፉ የሠ​ሩም ለፍ​ርድ ትን​ሣኤ ይነ​ሣሉ።


“እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሙታን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ልጅ ቃል የሚ​ሰ​ሙ​በት ሰዓት ይመ​ጣል፤ እር​ሱም አሁን ነው፤ የሚ​ሰ​ሙ​ትም ይድ​ናሉ።


አብ ሙታ​ንን እን​ደ​ሚ​ያ​ስ​ነ​ሣ​ቸው፥ ሕይ​ወ​ት​ንም እን​ደ​ሚ​ሰ​ጣ​ቸው እን​ዲሁ ወል​ድም ለሚ​ወ​ድ​ዳ​ቸው ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣል።


በአ​ባቱ ዕቅፍ ያለ አንድ ልጅ እርሱ ገለ​ጠ​ልን እንጂ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ከቶ ያየው የለም።


ሁሉ ከአ​ባቴ ዘንድ ተሰ​ጠኝ፤ ወልድ ማን እንደ ሆነ ከአብ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም፤ አብም ማን እንደ ሆነ ከወ​ልድ በቀር የሚ​ያ​ውቅ የለም። ወልድ ግን ለወ​ደ​ደው ይገ​ል​ጥ​ለ​ታል።”


እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።


ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።


ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፤ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios