ዮሐንስ 4:53 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱም፥ ጌታችን ኢየሱስ፥ “ልጅህ ድኖአል” ባለበት ሰዓት እንደ ሆነች ዐወቀ፤ እርሱም፥ ቤተ ሰቦቹም ሁሉ አመኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባትየውም ሰዓቱ ኢየሱስ፣ “ልጅህ በሕይወት ይኖራል” ያለበት ሰዓት መሆኑን ተገነዘበ፤ እርሱና ቤተ ሰቡም ሁሉ አመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቱም፥ ኢየሱስ “ልጅህ በሕይወት አለ፤” ባለው በዚያ ሰዓት እንደሆነ አወቀ፤ እርሱም ከቤተ ሰቦቹ ሁሉ ጋር አመነ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባትየውም ኢየሱስ “ልጅህ በሕይወት ይኖራል” ያለው በዚያኑ ሰዓት እንደ ሆነ ዐወቀ፤ ስለዚህ ከዚያን ቀን ጀምሮ እርሱና ቤተ ሰቡ ሁሉ በኢየሱስ አመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱም ኢየሱስ፦ ልጅህ በሕይወት አለ ባለው በዚያ ሰዓት እንደ ሆነ አወቀ፤ እርሱም ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር አመነ። |
እርስዋም ከቤተ ሰቦችዋ ጋር ተጠመቀች፤ “ለእግዚአብሔር አማኝ ካደረጋችሁኝስ ወደ ቤቴ ገብታችሁ እደሩ” ብላ ማለደችን፤ የግድም አለችን።
የምኵራብ አለቃ ቀርስጶስም ከነቤተ ሰቡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነ፤ ከቆሮንቶስ ሰዎችም ብዙዎች ሰምተው አምነው ተጠመቁ።