ዮሐንስ 4:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወደ አደረገበት የገሊላ ክፍል ወደምትሆን ወደ ቃና ዳግመኛ ሄደ። በቅፍርናሆም ልጁ የታመመበት የንጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ውሃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገበት፣ በገሊላ ወደምትገኘው ወደ ቃና ከተማ ዳግመኛ መጣ፤ በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት አንድ የቤተ መንግሥት ሹም ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም ውሃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት ወደ ገሊላ ቃና ዳግመኛ መጣ። በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት ከንጉሥ ቤት አንድ ሹም ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ውሃውን የወይን ጠጅ ወደ ለወጠባት በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ወደ ቃና ከተማ እንደገና ተመለሰ፤ በዚያን ጊዜ በቅፍርናሆም ልጁ የታመመበት አንድ የቤተ መንግሥት ሹም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወዳደረገባት ወደ ገሊላ ቃና ዳግመኛ መጣ። በቅፍርናሆምም ልጁ የታመመበት ከንጉሥ ቤት አንድ ሹም ነበረ። |
እርሱም፥ “በውኑ ባለ መድኀኒት ራስህን አድን፤ በቅፍርናሆም ያደረግኸውንና የሰማነውን ሁሉ በዚህም በሀገርህ ደግሞ አድርግ ብላችሁ ይህችን ምሳሌ ትመስሉብኛላችሁ” አላቸው።
ከዚህም በኋላ እርሱና እናቱ፥ ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ፤ በዚያም ብዙ ያይደለ ጥቂት ቀን ተቀመጡ።
ስምዖን ጴጥሮስ፥ ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ፥ ከገሊላ ቃና የሆነው ናትናኤል፥ የዘብዴዎስ ልጆችና ሌሎችም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት አብረው ነበሩ።