እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አልነበረም፤ ተጣራሁ፤ የሚመልስም አልነበረም፤ እጄ ለማዳን ጠንካራ አይደለምን? ወይስ ለማዳን አልችልምን? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዐሣዎቻቸው ይሞታሉ፤ በጥማትም ያልቃሉ።
ዮሐንስ 3:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባየውና በሰማው ይመሰክራል፤ ነገር ግን ምስክርነቱን የሚቀበለው የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያየውንና የሰማውን ይመሰክራል፤ ነገር ግን ምስክርነቱን ማንም አይቀበልም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፤ ምስክርነቱንም የሚቀበለው የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ያየውንና የሰማውን ይመሰክራል፤ ነገር ግን የእርሱን ምስክርነት የሚቀበል የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያየውንና የሰማውንም ይህን ይመሰክራል፥ ምስክሩንም የሚቀበለው የለም። |
እነሆ፥ መጣሁ፤ ሰውም አልነበረም፤ ተጣራሁ፤ የሚመልስም አልነበረም፤ እጄ ለማዳን ጠንካራ አይደለምን? ወይስ ለማዳን አልችልምን? እነሆ፥ በገሠጽሁ ጊዜ ባሕርን አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ምድረ በዳ አደርጋቸዋለሁ፤ ውኃም በማጣት ዐሣዎቻቸው ይሞታሉ፤ በጥማትም ያልቃሉ።
እንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባሪያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ እናንተን ግን ወዳጆች እላችኋለሁ፤ በአባቴ ዘንድ የሰማሁትን ሁሉ ነግሬአችኋለሁና።
ጲላጦስም፥ “እንግዲያ አንተ ንጉሥ ነህን?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “እኔ ንጉሥ እንደ ሆንሁ አንተ ራስህ ትላለህ፤ እኔ ስለዚህ ተወለድሁ፤ ስለዚህም ለእውነት ልመሰክር ወደ ዓለም መጣሁ፤ ከእውነት የሆነ ሁሉ ቃሌን ይሰማኛል” አለው።
እውነት እውነት እልሃለሁ፤ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ ነገር ግን ምስክርነታችንን አትቀበሉንም።
ወደ ዮሐንስም ሄደው፥ “መምህር ሆይ፥ በዮርዳኖስ ማዶ ካንተ ጋር የነበረው፥ አንተም የመሰከርህለት እርሱ እነሆ፥ ያጠምቃል፤ ሁሉም ወደ እርሱ ይሄዳል” አሉት።
ስለ እናንተ የምናገረውና የምፈርደው ብዙ አለኝ፤ የላከኝም እውነተኛ ነው፤ እኔ በእርሱ ዘንድ የሰማሁትን ለዓለም እናገራለሁ።”