La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 19:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አይ​ሁድ ግን የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበ​ርና፥ የዚ​ያች ሰን​በ​ትም ቀን ታላቅ ናትና “ሥጋ​ቸው በሰ​ን​በት በመ​ስ​ቀል ላይ አይ​ደር” አሉ፤ ጭን ጭና​ቸ​ው​ንም ሰብ​ረው ያወ​ር​ዷ​ቸው ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዕለቱ ለሰንበት መዘጋጃ ቀን ነበር። አይሁድ፣ የተሰቀሉት ሰዎች ሬሳ በሰንበት ቀን በመስቀል ላይ እንዳይውል ስለ ፈለጉና ያም የተለየ ሰንበት ስለ ነበር፣ የተሰቀሉት ሰዎች ጭናቸው ተሰብሮ በድናቸው እንዲወርድ ጲላጦስን ለመኑት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥ እንዲሁም ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና፥ ሥጋቸው በሰንበት ቀን በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ የአይሁድ ባለሥልጣኖች፥ የተሰቀሉትን ሰዎች ጭን ሰብረው፥ አስከሬናቸውን ከመስቀል እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት፤ ይህንንም ያደረጉበት ምክንያት የሰንበት ዝግጅት ቀን ስለ ነበረና ያ ሰንበትም ትልቅ በዓል ስለ ሆነ፥ በሰንበት ቀን ሥጋቸው በመስቀል ላይ እንዳይሆን ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 19:31
12 Referencias Cruzadas  

የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪቱ ቀን ቅድ​ስት ትባ​ላ​ላች፤ እን​ዲ​ሁም ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ቅድ​ስት ትሁ​ን​ላ​ችሁ፤ ለነ​ፍስ ከሚ​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ በቀር ማና​ቸ​ው​ንም ሥራ ሁሉ አት​ሥሩ


ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኃጥኣን ምሕረት ግን አለመመጽወት ነው።


የሕዝቤን ሥጋ በልታችኋል፥ ቁርበታቸውንም ገፍፋችኋቸዋል፥ አጥንታቸውንም ሰብራችኋል፥ ለአፍላል እንደሚሆን ሥጋ ለድስትም እንደሚሆን ሙዳ ቈራረጣችኋቸው።


በማግሥቱም ከመዘጋጀት በኋላ በሚሆነው ቀን፥ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ወደ ጲላጦስ ተሰበሰቡና


አሁንም በመሸ ጊዜ የሰንበት ዋዜማ የሆነ የማዘጋጀት ቀን ስለ ነበረ፥


ከዚ​ህም በኋላ ጲላ​ጦስ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይዞ ገረ​ፈው።


የፋ​ሲ​ካም የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበር፤ ጊዜ​ዉም ስድ​ስት ሰዓት ያህል ነበር፤ ጲላ​ጦ​ስም አይ​ሁ​ድን፥ “እነሆ፥ ንጉ​ሣ​ችሁ” አላ​ቸው፤


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም በዚያ ቀበ​ሩት፤ ለአ​ይ​ሁድ የመ​ሰ​ና​ዳት ቀን ነበ​ርና፤ መቃ​ብ​ሩም ለሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ቅርብ ነበር።


የጋ​ይ​ንም ንጉሥ በዝ​ግባ ዛፍ ላይ ሰቀ​ለው፤ እስከ ማታም ድረስ በዛፉ ላይ ቈየ። ፀሐ​ይም በገ​ባች ጊዜ ኢያሱ ያወ​ር​ዱት ዘንድ አዘዘ፤ ከዛ​ፉም አወ​ረ​ዱት፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም በር አደ​ባ​ባይ ጣሉት፤ በላ​ዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለ​ውን ታላቅ የድ​ን​ጋይ ክምር ከመ​ሩ​በት።