አብርሃምም የመሥዋዕቱን ዕንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱም እሳቱንና ቢላዋዉን በእጁ ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ።
ዮሐንስ 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው ቀራንዮ ወደሚባል ቦታ ወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም የራሱን መስቀል ተሸክሞ በአራማይክ “ጎልጎታ” ተብሎ ወደሚጠራው “የራስ ቅል” ወደተባለው ቦታ ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መስቀሉንም ተሸክሞ የራስ ቅል ወደሚሉት ስፍራ፥ በዕብራይስጥም ጎልጎታ ወደ ተባለው ቦታ ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢየሱስ መስቀሉን ተሸክሞ፥ “የራስ ቅል” ወደሚባለው ስፍራ ወጣ፤ ይህ ስፍራ በዕብራይስጥ ቋንቋ “ጎልጎታ” ይባላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀሉንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደ ተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ። |
አብርሃምም የመሥዋዕቱን ዕንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱም እሳቱንና ቢላዋዉን በእጁ ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ።
እነሆም፥ አንድ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ መጥቶ፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ይህን ብዙ ሕዝብ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እንግዲህ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ” አለው።
“ተሳዳቢውን ከሰፈር ወደ ውጭ አውጣው፤ የሰሙትም ሁሉ እጃቸውን በራሱ ላይ ይጫኑበት፤ ማኅበሩም ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት።”
ኢየሱስም ወደ እርሱ ተመልክቶ ወደደውና “አንድ ነገር ጐደለህ፤ ሂድ፤ ያለህን ሁሉ ሽጠህ ለድሆች ስጥ፤ በሰማይም መዝገብ ታገኛለህ፤ መስቀሉንም ተሸክመህ ና፤ ተከተለኝ፤” አለው።
በወሰዱትም ጊዜ የቀሬና ሰው ስምዖንን ከዱር ሲመለስ ያዙት፤ ከጌታችን ከኢየሱስም በስተኋላ መስቀሉን አሸከሙት።
ቀራንዮ ወደሚባለው ቦታ በደረሱ ጊዜም፥ በዚያ ሰቀሉት፤ እነዚያንም ሁለት ወንበዴዎች አንዱን በቀኙ አንዱንም በግራው ሰቀሉ።
በራስጌውም ደብዳቤ ጻፉ፤ ጽሕፈቱም በሮማይስጥ፥ በጽርዕና በዕብራይስጥ ሆኖ “የአይሁድ ንጉሣቸው ይህ ነው” የሚል ነበር።
ሁሉንም እንዲህ አላቸው፥ “ሊከተለኝ የሚወድ ሰው ራሱን ይካድ፤ ጨክኖም የሞቱን መስቀል ይሸከም፤ ዕለት ዕለትም ይከተለኝ።
ጲላጦስም ይህን ሰምቶ ጌታችን ኢየሱስን ወደ ውጭ አወጣው፤ በዕብራይስጥም ገበታ ተብሎ በሚጠራው “ጸፍጸፍ” በሚሉት ቦታ ላይ በወንበር ተቀመጠ።
በኢየሩሳሌምም በበጎች በር አጠገብ መጠመቂያ ነበረች፤ ስምዋንም በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ይሉአታል፤ አምስት እርከኖችም ነበሩአት።
ከከተማም ወደ ውጭ ጐትተው አውጥተው ወገሩት፤ የሚወግሩት ሰዎችም ልብሳቸውን ሳውል በሚባል ጐልማሳ እግር አጠገብ አስቀመጡ።