ዮሐንስ 18:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም በምን ዐይነት ሞት ይሞት ዘንድ እንዳለው ሲያመለክት የተናገረው የጌታችን የኢየሱስ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ የሆነው በምን ዐይነት ሞት እንደሚሞት ለማመልከት ሲል ኢየሱስ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ኢየሱስ በምን ዓይነት ሞት እንደሚሞት ሲያመለክት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነብር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሆነው ኢየሱስ በምን ዐይነት ሞት እንደሚሞት የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስ በምን ዓይነት ሞት ሊሞት እንዳለው ሲያመለክት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው። |
“እነሆ፥ ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን፤ የሰው ልጅም ለካህናት አለቆችና ለጻፎች አልፎ ይሰጣል፤ የሞት ፍርድም ይፈርዱበታል፤ ለአሕዛብም አሳልፈው ይሰጡታል፤
አይሁድም፥ “አንተ፥ ሰው ስትሆን ራስህን እግዚአብሔርን ታደርጋለህና፤ ስለ መሳደብህ ነው እንጂ ስለ መልካም ሥራህስ አንወግርህም” አሉት።
ነገር ግን ይህን የምናገር ስለ ሁላችሁ አይደለም፤ የመረጥኋቸው እነማን እንደ ሆኑ እኔ አውቃለሁ፤ ነገር ግን መጽሐፍ ‘እንጀራዬን የሚመገብ ተረከዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈጸም ዘንድ ነው።
ጲላጦስም፥ “እናንተ ወስዳችሁ እንደ ሕጋችሁ ፍረዱበት” አላቸው፤ አይሁድም፥ “እኛስ ማንንም ልንገድል አልተፈቀደልንም” አሉት።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ በአደረጋችሁት ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ያንጊዜ ታውቃላችሁ፤ አባቴ እንደ አስተማረኝም እንዲሁ እናገራለሁ እንጂ የምናገረው ከእኔ አይደለም።
እኛንስ ክርስቶስ ስለ እኛ የኦሪትን መርገም በመሸከሙ ከኦሪት መርገም ዋጅቶናል፤ መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “በእንጨት ላይ የተሰቀለ ሁሉ ርጉም ነው።”
በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሥጋው በእንጨት ላይ አይደር፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር እንዳታረክስ በእርግጥ በዚያው ቀን ቅበረው።