በምክራቸው ሰውነቴ አትገናኛቸው፤ ዐሳቤም በአመፃቸው አትተባበርም፤ በቍጣቸው ሰውን ገድለዋልና፤ በገዛ ፈቃዳቸውም የሀገርን ሥር ቈርጠዋልና።
ዮሐንስ 18:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮችና ሎሌዎችም በዚያ ቆመው እሳት አንድደው ይሞቁ ነበር፤ የዚያች ሌሊት ብርድ ጽኑ ነበርና፤ ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋር ቆሞ ይሞቅ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብርድ ስለ ነበር ባሮቹና ጠባቂዎቹ ባያያዙት የከሰል ፍም ዙሪያ ለመሞቅ ቆመው ሳሉ፣ ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋራ ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይበርድ ነበረና አገልጋዮችና ሎሌዎች የከሰል እሳት አንድደው ቆመው ይሞቁ ነበር፤ ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋር ቆሞ ይሞቅ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጊዜው ብርድ ስለ ነበረ አገልጋዮቹና የዘብ ኀላፊዎች የከሰል እሳት አንድደው ቆመው ይሞቁ ነበር፤ ጴጥሮስም ከእነርሱ ጋር ቆሞ ይሞቅ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብርድ ነበረና ባሮችና ሎሌዎች የፍም እሳት አንድደው ቆሙ ይሞቁም ነበር፤ ጴጥሮስም ደግሞ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ይሞቅ ነበር። |
በምክራቸው ሰውነቴ አትገናኛቸው፤ ዐሳቤም በአመፃቸው አትተባበርም፤ በቍጣቸው ሰውን ገድለዋልና፤ በገዛ ፈቃዳቸውም የሀገርን ሥር ቈርጠዋልና።
እዚያም ወዳለ ዋሻ ገባ፤ በዚያም አደረ፤ እነሆም፥ “ኤልያስ ሆይ! ምን አመጣህ?” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ እርሱ መጣ።
ምስጉን ነው፥ በዝንጉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኀጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው።
ስምዖን ጴጥሮስም ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፤ “አንተስ ከእርሱ ደቀ መዛሙርት ወገን አይደለህምን?” አሉት፤ እርሱም፥ “አይደለሁም” ብሎ ካደ።
ይሁዳም ከካህናት አለቆችና ከፈሪሳውያን ወታደሮችን ተቀበለ፤ ሎሌዎቻቸውንም በረዳትነት ወሰደ፤ ፋኖስና የችቦ መብራት፥ የጦር መሣሪያም ይዞ ወደዚያ ሄደ።