ዮሐንስ 18:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀያፋም “ስለ ሕዝቡ ሁሉ አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል” ብሎ አይሁድን የመከራቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀያፋም ለሕዝቡ ሲባል አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል ብሎ አይሁድን የመከረ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀያፋም “ስለ ሕዝቡ ሲባል አንድ ሰው ቢሞት ይሻላል” ሲል አይሁድን የመከራቸው ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀያፋ “አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ቢሞት የተሻለ ነው” ሲል የአይሁድ ባለሥልጣኖችን የመከረ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀያፋም፦ “አንድ ሰው ስለ ሕዝብ ይሞት ዘንድ ይሻላል” ብሎ ለአይሁድ የመከራቸው ነበረ። |
ያም ወደብ ክረምቱን ሊከርሙበት የማይመች ነበር፤ ስለዚህም ብዙዎች ከዚያ ይወጡ ዘንድ ይቻላቸው እንደ ሆነ በቀኝ በኩል ወደ አለው ፊንቄ ወደሚባለው ወደ ሁለተኛው የቀርጤስ ወደብ ይደርሱ ዘንድ ወደዱ።
በዚያም ብዙ ቀን ቈየን፤ የአይሁድም የጾም ወራት አልፎ ስለ ነበረ በመርከብ ለመሄድ የሚያስፈራ ነበርና ጳውሎስ እንዲህ ብሎ መከራቸው።