Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 27:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ያም ወደብ ክረ​ም​ቱን ሊከ​ር​ሙ​በት የማ​ይ​መች ነበር፤ ስለ​ዚ​ህም ብዙ​ዎች ከዚያ ይወጡ ዘንድ ይቻ​ላ​ቸው እንደ ሆነ በቀኝ በኩል ወደ አለው ፊንቄ ወደ​ሚ​ባ​ለው ወደ ሁለ​ተ​ኛው የቀ​ር​ጤስ ወደብ ይደ​ርሱ ዘንድ ወደዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ክረምቱንም በዚያ ለማሳለፍ ወደቡ አመቺ ስላልነበረ፣ አብዛኛዎቹ ፍንቄ ወደተባለው ወደብ ደርሰው በዚያ ለመክረም ተስፋ በማድረግ ጕዟችንን እንድንቀጥል ውሳኔ አስተላለፉ፤ ወደቡም በቀርጤስ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ትይዩ የሚገኝ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ያም ወደብ ይከርሙበት ዘንድ የማይመች ስለ ሆነ፥ የሚበዙቱ ቢቻላቸው በሰሜንና በደቡብ ምዕራብ ትይዩ ወዳለው ፍንቄ ወደሚሉት ወደ ቀርጤስ ወደብ ደርሰው ይከርሙ ዘንድ ከዚያ እንዲነሡ መከሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ያ ወደብ ለክረምት ማሳለፊያ ምቹ ስላልነበረ አብዛኞቹ ሰዎች “ጒዞአቸውን ቀጥለው የሚቻል ቢሆን በሰሜን ምዕራብና በደቡብ ምዕራብ በር ወዳለው ፊንቄ ወደሚባለው የቀርጤስ ወደብ ደርሰን ክረምቱን እዚያ እናሳልፍ” ብለው አሳብ አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ያም ወደብ ይከርሙበት ዘንድ የማይመች ስለ ሆነ፥ የሚበዙቱ ቢቻላቸው በሰሜንና በደቡብ ምዕራብ ትይዩ ወዳለው ፍንቄ ወደሚሉት ወደ ቀርጤስ ወደብ ደርሰው ይከርሙ ዘንድ ከዚያ እንዲነሡ መከሩ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 27:12
8 Referencias Cruzadas  

ከቀ​ር​ጤ​ስና ከዐ​ረ​ብም የመ​ጣን፥ እነሆ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጌት​ነት በየ​ሀ​ገ​ራ​ችን ቋንቋ ሲና​ገሩ እን​ሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለን።”


ልከኛ የአ​ዜብ ነፋ​ስም ነፈሰ፤ እነ​ር​ሱም እንደ ወደዱ የሚ​ደ​ርሱ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበር፤ መል​ሕ​ቁ​ንም አነሡ፤ በቀ​ር​ጤ​ስም አጠ​ገብ ሄዱ።


ከእ​ኛም መብል የበላ አል​ነ​በ​ረም። ጳው​ሎ​ስም ተነ​ሥቶ በመ​ካ​ከል ቆመና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ ሰዎች ሆይ፥ ቀድሞ ቃሌን ሰም​ታ​ች​ሁኝ ቢሆን ከቀ​ር​ጤ​ስም ባት​ወጡ ኖሮ ከዚህ ጕዳ​ትና መከራ በዳ​ና​ችሁ ነበር።


ብዙ ቀንም እያ​ዘ​ገ​ምን ሄድን፤ በጭ​ን​ቅም ወደ ቀኒ​ዶስ አን​ጻር ደረ​ስን፤ ወደ​ዚ​ያም በቀ​ጥታ ለመ​ድ​ረስ ነፋስ ቢከ​ለ​ክ​ለን በቀ​ር​ጤስ በኩል በሰ​ል​ሙና ፊት ለፊት ዐለ​ፍን።


ባጠ​ገ​ብ​ዋም በጭ​ንቅ ስና​ልፍ ላሲያ ለም​ት​ባ​ለው ከተማ አቅ​ራ​ቢያ ወደ ሆነ​ችው መል​ካም ወደብ ወደ​ም​ት​ባ​ለው ቦታ ደረ​ስን።


የገዛ ራሳቸው ነቢይ የሆነ ከእነርሱ አንዱ “የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው፤” ብሎአል።


ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos