ጌታችን ኢየሱስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ ባወቀ ጊዜ፥
ዮሐንስ 16:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን ግን ወደ ላከኝ ወደ አብ እሄዳለሁ፤ ከእናንተ አንዱ እንኳ፦ ‘ወዴት ትሄዳለህ?’ ብሎ አይጠይቀኝም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንግዲህ ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤ ይሁን እንጂ ከእናንተ፣ ‘የምትሄደው የት ነው?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ፤ ከእናንተም ‘ወዴት ትሄዳለህ?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን ወደ ላከኝ መሄዴ ነው፤ ሆኖም ከእናንተ ‘ወዴት ትሄዳለህ?’ ብሎ የሚጠይቀኝ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን ግን ወደ ላከኝ እሄዳለሁ ከእናንተም፦ “ወዴት ትሄዳለህ?” ብሎ የሚጠይቀኝ የለም። |
ጌታችን ኢየሱስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ ባወቀ ጊዜ፥
ስምዖን ጴጥሮስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ወዴት ትሄዳለህ?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፤ ኋላ ግን ትከተለኛለህ” አለው።
እኔ እንደምሄድ ወደ እናንተም እንደምመለስ የነገርኋችሁን ሰምታችኋል፤ ብትወዱኝስ ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር፤ እርሱ አብ ይበልጠኛልና።
ደቀ መዛሙርቱም እርስ በርሳቸው፥ “ጥቂት ጊዜ አለ፤ አታዩኝምም፤ ደግሞም ጥቂት ጊዜ አለ፤ እንደገናም ታዩኛላችሁ፥ ወደ አብ እሄዳለሁና የሚለን ይህ ነገር ምንድነው?” ተባባሉ።
እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የመልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።
የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ፥ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።