“እኔ ንጹሕ ነኝና ከእኔ ራቁ፥ ወደ እኔም አትቅረቡ” ይላሉ። ስለዚህም የቍጣዬ ጢስ በዘመኑ ሁሉ እንደ እሳት ይነድድባቸዋል።
ዮሐንስ 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ደግሞም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚያቀርብ የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምኵራብ ያስወጧችኋል፤ እንዲያውም የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንዳገለገለ የሚቈጥርበት ጊዜ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከምኲራቦች አስወጥተው ያባርሩአችኋል፤ እንዲያውም እናንተን የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን የሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከምኵራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል። |
“እኔ ንጹሕ ነኝና ከእኔ ራቁ፥ ወደ እኔም አትቅረቡ” ይላሉ። ስለዚህም የቍጣዬ ጢስ በዘመኑ ሁሉ እንደ እሳት ይነድድባቸዋል።
በቃሉ የምትንቀጠቀጡ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፥ “የእግዚአብሔር ስም ይከብር ዘንድ፦ ደስታችሁም ይገለጥ ዘንድ፥ እነርሱም ያፍሩ ዘንድ የሚጠሏችሁንና የሚጸየፉአችሁን ወንድሞቻችን በሏቸው።
ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ቢጠሉአችሁ፥ ከሰው ለይተው ቢአሳድዱአችሁ፥ ቢሰድቡአችሁ፥ ክፉ ስምም ቢአወጡላችሁ ብፁዓን ናችሁ።
ከሕዝቡ አለቆችም ያመኑበት ብዙዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ከምኵራብ አስወጥተው እንዳይሰዱአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም።
“ዛሬስ በምሳሌ ነገርኋችሁ፤ ነገር ግን የአብን ነገር ገልጬ እነግራችኋለሁ እንጂ ለእናንተ በምሳሌ የማልናገርበት ጊዜ ይመጣል።
እያንዳንዳችሁ በየቦታዉ የምትበታተኑበት፥ እኔንም ብቻዬን የምትተዉበት ጊዜ ይደርሳል፤ ደርሶአልም፤ እኔ ግን ብቻዬን አይደለሁም፤ አብ ከእኔ ጋር ነውና።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላት፥ “አንቺ ሴት በዚህ ተራራ ወይም በኢየሩሳሌም ብቻ ለአብ የማይሰግዱበት ሰዓት እንደምትመጣ እመኝኝ።
ነገር ግን በእውነት የሚሰግዱ በመንፈስና በእውነት ለአብ የሚሰግዱባት ጊዜ ትመጣለች፤ እርስዋም አሁን ናት። አብ እንዲህ የሚሰግዱለትን ይሻልና።
ወላጆቹ አይሁድን ስለ ፈሩ ይህን አሉ፥ “እርሱ ክርስቶስ ነው ብሎ በእርሱ የሚያምን ቢኖር ከምኵራብ ይውጣ” ብለው አይሁድ ተስማምተው ነበርና።
የከተማዉም ሰዎች ኢዮአስን፥ “የበዓልን መሠዊያ አፍርሶአልና፥ በዙሪያውም ያለውን የማምለኪያ ዐጸድ ቈርጦአልና ይገደል ዘንድ ልጅህን አምጣ” አሉት።