ዮሐንስ 16:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንዳትሰናከሉ ይህን ነገርኋችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን ሁሉ የነገርኋችሁ እንዳትሰናከሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንዳትሰናከሉ ይህን ነግሬአችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እነሆ፥ ይህን ሁሉ የነገርኳችሁ እምነታችሁ እንዳይናወጥ ብዬ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳትሰናከሉ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። |
ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ እኔ እንደ ነገርኋችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ነገርኋችሁ። አስቀድሜ ግን ይህን አልነገርክኋችሁም ነበር፤ ከእናንተ ጋር ነበርሁና።
የሚሻለውን ሥራ እንድትመረምሩና እንድትፈትኑ፥ ክርስቶስ በሚመጣበት ቀን ያለ ዕንቅፋት ቅዱሳን ትሆኑ ዘንድ፦