ዮሐንስ 12:38 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አቤቱ፥ ምስክርነታችንን ማን ያምነናል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?” ያለው የነቢዩ የኢሳይያስ ቃል ይደርስ ዘንድ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም ነቢዩ ኢሳይያስ፣ “ጌታ ሆይ፤ መልእክታችንን ማን አምኗል? የጌታስ ክንድ ለማን ተገልጧል?” ያለው ቃል እንዲፈጸም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ነቢዩ ኢሳይያስ “ጌታ ሆይ! ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ?” ብሎ የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስ፥ “ጌታ ሆይ! ምስክርነታችንን ማን አመነ? የጌታስ ኀይል ለማን ተገለጠ?” ሲል የተናገረው ቃል እንዲፈጸም ነው። |
ጽድቄ ፈጥና ትመጣለች፤ ማዳኔም እንደ ብርሃን ትደርሳለች፤ አሕዛብ በክንዴ ይታመናሉ፤ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤ በክንዴም ይታመናሉ።
እኔ በዓለም ከእነርሱ ጋር ሳለሁ ግን የሰጠኸኝን በስምህ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም፤ የመጽሐፉም ቃል ይፈጸም ዘንድ ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ አንድ ስንኳን አልጠፋም።
እርስ በርሳቸውም፥ “ዕጣ እንጣጣልና ለደረሰ ይድረሰው እንጂ አንቅደደው ተባባሉ፤” ይህም “ልብሶችን ለራሳቸው ተካፈሉ፤ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ” ያለው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው፤ ጭፍሮችም እንዲሁ አደረጉ።
ነገር ግን ሁሉም የወንጌልን ትምህርት የሰሙ አይደለም፤ ኢሳይያስም፥ “አቤቱ፥ ምስክርነታችንንስ ማን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንዱ ለማን ተገለጠ?” ብሎአልና።
ለእኛ ለዳንነው ግን ከአይሁድ፥ ከአረሚም ብንሆን ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ የእግዚአብሔርም ጥበብ ነው።
በስሙም ለአሕዛብ ወንጌልን አስተምር ዘንድ፥ በእጄም የልጁ ክብር ይታወቅ ዘንድ ልጁን ገለጠልኝ፤ ያንጊዜም ከሥጋዊና ከደማዊ ሰው ጋር አልተማከርሁም።