La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 11:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ጉባ​ኤ​ውን ሰብ​ስ​በው እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እነሆ፥ ይህ ሰው ብዙ ተአ​ም​ራት ያደ​ር​ጋል፤ ምን እና​ድ​ርግ?

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን የአይሁድን ሸንጎ ስብሰባ ጠሩ። እነርሱም እንዲህ አሉ፤ “ይህ ሰው ብዙ ታምራዊ ምልክቶችን እያደረገ ስለ ሆነ ምን ብናደርግ ይሻላል?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ሸንጎ ሰብስበው እንዲህ አሉ፥ “ምን እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶችን ያደርጋልና።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን የሸንጎውን አባሎች ሰብስበው እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው ብዙ ተአምራት ስለሚያደርግ ምን ብናደርግ ይሻላል?

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንግዲህ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያን ሸንጎ ሰብስበው፦ “ምን እናድርግ? ይህ ሰው ብዙ ምልክቶች ያደርጋል።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 11:47
17 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ የካህናት አለቆች የሕዝብም ሽማግሎች ቀያፋ በሚባለው በሊቀ ካህናቱ ግቢ ተሰበሰቡ፤


እኔ ግን እላችኋለሁ፤በወንድሙ ላይ የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙንም ጨርቃም የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ደንቆሮ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።


ከሁለት ቀን በኋላ ፋሲካና የቂጣ በዓል ነበረ። የካህናት አለቆችም ጻፎችም እንዴት አድርገው በተንኰል እንደሚይዙትና እንደሚገድሉት ይፈልጉ ነበር።


የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ጻፎ​ችም ሊገ​ድ​ሉት ይሹ ነበር፤ ነገር ግን ሕዝ​ቡን ይፈ​ሩ​አ​ቸው ነበር።


የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ያለ​በ​ትን የሚ​ያ​ውቅ ቢኖር ይይ​ዙት ዘንድ እን​ዲ​ያ​መ​ለ​ክ​ታ​ቸው አዘዙ።


ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም እርስ በር​ሳ​ቸው፥ “የም​ታ​ገ​ኙት ምንም ጥቅም እን​ደ​ሌለ ታያ​ላ​ች​ሁን? እነሆ፥ ዓለም ሁሉ ተከ​ት​ሎ​ታል” ተባ​ባሉ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በቃና ዘገ​ሊላ ያደ​ረ​ገው የተ​አ​ም​ራት መጀ​መ​ሪያ ይህ ነው፤ ክብ​ሩ​ንም ገለጠ፤ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም አመ​ኑ​በት።


በበ​ሽ​ተ​ኞ​ችም ላይ ያደ​ረ​ገ​ውን ተአ​ም​ራት ስለ አዩ ብዙ ሰዎች ተከ​ተ​ሉት፤


ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ሕዝቡ በእ​ርሱ ምክ​ን​ያት እንደ አጕ​ረ​መ​ረሙ ሰሙ፤ የካ​ህ​ናት አለ​ቆ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ይይ​ዙት ዘንድ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውን ላኩ።


ሎሌ​ዎ​ቹም ወደ ካህ​ናት አለ​ቆ​ችና ወደ ፈሪ​ሳ​ው​ያን ተመ​ለሱ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ያላ​መ​ጣ​ች​ሁት ለም​ን​ድን ነው?” አሉ​አ​ቸው።


ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ጥዋት ገስ​ግ​ሠው ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገቡና አስ​ተ​ማሩ፤ ሊቀ ካህ​ና​ቱና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩት ግን ጉባ​ኤ​ው​ንና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን ሁሉ ሰበ​ሰቡ፤ ሐዋ​ር​ያ​ት​ንም ያመ​ጡ​አ​ቸው ዘንድ ወደ ወኅኒ ቤት ላኩ።


ሊቃነ ካህ​ና​ትና የቤተ መቅ​ደሱ ሹምም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ፥ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን አጥ​ተው፥ “እንጃ ይህ ምን ይሆን?” አሉ።