La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዮሐንስ 1:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ፊል​ጶ​ስም ናት​ና​ኤ​ልን አገ​ኘ​ውና፥ “ሙሴ በኦ​ሪት፥ ነቢ​ያ​ትም ስለ እርሱ የጻ​ፉ​ለ​ትን የዮ​ሴ​ፍን ልጅ የና​ዝ​ሬ​ቱን ኢየ​ሱ​ስን አገ​ኘ​ነው” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ናትናኤልም፣ “ከናዝሬት በጎ ነገር ሊወጣ ይችላልን?” አለ። ፊልጶስም፣ “መጥተህ እይ” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ናትናኤልም “ከናዝሬት መልካም ነገር ሊወጣ ይችላልን?” አለው። ፊልጶስ “መጥተህ እይ” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ናትናኤል ግን፥ “ከናዝሬት መልካም ነገር ከቶ ሊገኝ ይችላልን?” አለው። ፊልጶስም “መጥተህ እይ!” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ፊልጶስ ናትናኤልን አግኝቶ፦ ሙሴ በሕግ ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል አለው።

Ver Capítulo



ዮሐንስ 1:46
14 Referencias Cruzadas  

ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥


በነቢያት “ናዝራዊ ይባላል” የተባለው ይፈጸም ዘንድ፥ ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ።


እና​ንተ ራሳ​ችሁ እው​ነ​ቱን ለምን አት​ፈ​ር​ዱም?


በማ​ግ​ሥ​ቱም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ገሊላ ሊሄድ ወደደ፤ ፊል​ጶ​ስ​ንም አገ​ኘ​ውና “ተከ​ተ​ለኝ” አለው።


ፊል​ጶስ ግን ከእ​ን​ድ​ር​ያ​ስና ከጴ​ጥ​ሮስ ከተማ ከቤተ ሳይዳ ነበር።


እነ​ር​ሱም ከገ​ሊላ፥ የቤተ ሳይዳ ሰው ወደ ሆነው ወደ ፊል​ጶስ ሄደው፥ “አቤቱ፥ ጌታ ኢየ​ሱ​ስን ልና​የው እን​ወ​ድ​ዳ​ለን” ብለው ለመ​ኑት።


ፊል​ጶ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ አብን አሳ​የ​ንና ይበ​ቃ​ናል” አለው።


“የሠ​ራ​ሁ​ትን ሁሉ የነ​ገ​ረ​ኝን ሰው ታዩ ዘንድ ኑ፤ እንጃ፥ እርሱ ክር​ስ​ቶስ ይሆን?”


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ዐይ​ኖ​ቹን አን​ሥቶ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ሲመጡ አየና ፊል​ጶ​ስን፥ “ለእ​ነ​ዚህ ሰዎች የም​ና​በ​ላ​ቸው እን​ጀራ ከወ​ዴት እን​ግዛ?” አለው።


ፊል​ጶ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “ከእ​ነ​ርሱ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ጥቂት ጥቂት ይወ​ስዱ ዘንድ የሁ​ለት መቶ ዲናር እን​ጀራ አይ​በ​ቃ​ቸ​ውም።”


እነ​ር​ሱም መል​ሰው፥ “አን​ተም ደግሞ ከገ​ሊላ ነህን? ከገ​ሊላ ነቢይ እን​ደ​ማ​ይ​ነሣ መር​ም​ርና እይ” አሉት።