ኢዩኤል 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፥ ፈጥናችሁ ኑ፥ ተሰብሰቡ፤ የዋሃንም ሰልፈኞች ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ በዙሪያ ያላችሁ ሕዝቦች ሁላችሁ፤ ፈጥናችሁ ኑ፤ በዚያም ተሰብሰቡ። እግዚአብሔር ሆይ፤ ተዋጊዎችህን ወደዚያ አውርድ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፥ ቸኩላችሁ ኑ፥ ተሰብሰቡ፥ አቤቱ፥ ኃያላኖችህን ወደዚያ አውርድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፤ በፍጥነት ውጡ! በሸለቆውም ተሰብሰቡ።” እግዚአብሔር ሆይ፥ ተዋጊ ሠራዊትህን ላክ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ በዙሪያ ያላችሁ አሕዛብ ሁሉ፥ ቸኵላችሁ ኑ፥ ተሰብሰቡ፥ አቤቱ፥ ኃያላኖችህን ወደዚያ አውርድ። |
እኔ አዝዤ ቅዱሳኔን አመጣቸዋለሁ፤ ኀያላኔንም አመጣቸዋለሁ፤ ደስ እያላቸውም ይመጣሉ፤ ቍጣዬንም ይፈጽማሉ፤ ያዋርዱአቸዋልም።
የእግዚአብሔርም መልአክ ወጣ፤ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ሰዎችን ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉም በድኖች ሆነው አገኙአቸው።
አሕዛብን ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል በተበተኑበትና ምድሬን በተካፈሉበት በዚያ ስለ ወገኖች ስለ ርስቴ ስለ እስራኤል እወቅሳቸዋለሁ።
መዓቴንና የቍጣዬን ትኵሳት ሁሉ አፈስስባቸው ዘንድ ፍርዴ አሕዛብን ለመሰብሰብ፥ መንግሥታትንም ለማከማቸት ነውና፥ ምድርም ሁሉ በቅንዓቴ እሳት ትበላለችና ስለዚህ ለመበዝበዝ እስከምነሣበት ቀን ድረስ ጠብቁኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።