ኢዩኤል 2:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ ሕዝቤም ለዘለዓለም አያፍርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እኔ በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፣ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፣ እንደ እኔም ያለ፣ ሌላ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ ሕዝቤም ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔም ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ፥ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ፥ ሕዝቤም ለዘለዓለም አያፍርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤ ሆይ! እኔ በመካከላችሁ እንዳለሁ፥ አምላካችሁም እኔ ብቻ እንደ ሆንኩና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ፤ ሕዝቤ ከእንግዲህ ወዲህ ኀፍረት አይደርስባቸውም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም በእስራኤል መካከል እንዳለሁ፥ እኔም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ታውቃላችሁ፥ ሕዝቤም ለዘላለም አያፍርም። |
በደረቅ መሬት ላይ ለሚሄድና ለተጠማ ውኃን እሰጣለሁ፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ፥ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አኖራለሁ፤
ራሳችሁን አትደብቁ፤ ከጥንት ጀምሮ አልሰማችሁምን? አልነገርኋችሁምን? ከእኔ ሌላ አምላክ እንደ ሌለ ምስክሮች ናችሁ።”
ሰማይን የፈጠረ እግዚአብሔር፥ እርሱም ምድርን የሠራና ያደረገ ያጸናትም፥ መኖሪያም ልትሆን እንጂ ለከንቱ እንድትሆን ያልፈጠራት አምላክ፥ እንዲህ ይላል፥ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።
በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ያውቁ ዘንድ እኔ እግዚአብሔር አምላክ ነኝ፤ ከእኔም ሌላ አምላክ የለም።
እኔ አምላክ ነኝና፤ ያለ እኔም ሌላ የለምና የቀድሞውንና የጥንቱን ነገር ዐስቡ። እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።
ነገሥታትም አሳዳጊዎች አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።”
እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም ስለ ኀጢአታችን ለሞት አሳልፎ ሰጠው።
ጅማትንም እሰጣችኋለሁ፤ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ፤ በእናንተም ላይ ቍርበትን እዘረጋለሁ፤ ትንፋሽንም አገባባችኋለሁ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
እኔም ወደ አሕዛብ አስማርኬአቸዋለሁና፥ ወደ ገዛ ምድራቸውም ሰብስቤአቸዋለሁና እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ በዚያም ከእነርሱ አንድ ሰው ከእንግዲህ ወዲያ አላስቀርም፤
ፊቴንም ከእነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ አልመልስም፤ መዓቴን በእስራኤል ቤት ላይ አፍስሻለሁና፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ብዙ መብል ትበላላችሁ፤ ትጠግቡማላችሁ፤ ከእናንተም ጋር ተአምራትን የሠራውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ስም ታመሰግናላችሁ፤ ሕዝቤም ለዘለዓለም አያፍርም።
“እኔም በተቀደሰ ተራራዬ በጽዮን የምቀመጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ ያን ጊዜም ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ከተማ ትሆናለች፥ እንግዶችም ከእንግዲህ ወዲህ አያልፉባትም።
በዚያን ጊዜ እየታበዩ የሚፎክሩትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኰሪምና በዚያ ቀን በእኔ ላይ ተላልፈሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም።
አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።
ሙሴም “የእግዚአብሔር ሕዝብ ሁሉ ነቢያት ቢሆኑ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ መንፈሱን ቢያሳድር አንተ ስለ እኔ ትቀናለህን?” አለው።
በያዕቆብ ላይ ድካም የለም፤ በእስራኤልም ሕማም አይታይም፤ አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነው፤ የአለቆችም ክብር ለእርሱ ነው።
የእግዚአብሔርን ታቦትስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው? የሕያው እግዚአብሔር ማደሪያዎች እኛ አይደለንምን? እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረ፥ “እኔ በእነርሱ አድራለሁ፤ በመካከላቸውም እኖራለሁ፤ አምላካቸውም እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆኑኛል።”
አምላክህ እግዚአብሔር ሊያድንህ፥ ጠላቶችህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈርህ ውስጥ ይሄዳልና ስለዚህ ነውረኛ ነገር እንዳያይብህ፥ ፊቱንም ከአንተ እንዳይመልስ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን።
ታላቅም ድምፅ ከሰማይ “እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤