Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 45:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በፀ​ሐይ መው​ጫና በም​ዕ​ራብ ያሉ ከእኔ በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ያውቁ ዘንድ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም ሌላ አም​ላክ የለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ይኸውም ሰዎች ከፀሓይ መውጫ፣ እስከ መጥለቂያው፣ ከእኔ በቀር ሌላ እንደሌለ እንዲያውቁ ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ ሌላ ማንም የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በፀሐይ መውጫና በምዕራብ ያሉ፥ ከእኔ በቀር ማንም ሌላ እንደሌለ ይወቁ እኔ ጌታ ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ይህንንም የማደርገው መላው ዓለም እኔ ብቻ እግዚአብሔር እንደ ሆንኩና ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ ያውቅ ዘንድ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 45:6
16 Referencias Cruzadas  

ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነኝ፤ ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ የለም፤ አጸ​ና​ሁህ፤ አንተ ግን አላ​ወ​ቅ​ኸ​ኝም።


እን​ግ​ዲህ አም​ላ​ካ​ችን አቤቱ፥ የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ሁሉ አንተ ብቻ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንህ ያውቁ ዘንድ ከእጁ አድ​ነን።”


ታላቅ እሆ​ና​ለሁ፤ እቀ​ደ​ስ​ማ​ለሁ፤ እመ​ሰ​ገ​ና​ለ​ሁም፤ በብዙ አሕ​ዛ​ብም ዐይን የታ​ወ​ቅሁ እሆ​ና​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


“ክብ​ሬ​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ አሕ​ዛ​ብም ሁሉ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ፍር​ዴን፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያኖ​ር​ኋ​ትን እጄን ያያሉ።


እነ​ር​ሱም አይ​ጐ​ዱ​ትም፤ በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራዬ ሁሉ ላይ ማን​ንም አይ​ጐ​ዱም፤ አያ​ጠ​ፉ​ምም፤ ብዙ ውኃ ባሕ​ርን እን​ደ​ሚ​ሸ​ፍን ምድር እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በማ​ወቅ ትሞ​ላ​ለ​ችና።


ታው​ቁና ታም​ኑ​ብኝ ዘንድ እኔም እንደ ሆንሁ ታስ​ተ​ውሉ ዘንድ፥ እና​ንተ፥ የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትም ባሪ​ያዬ ምስ​ክ​ሮች ሁኑ፤ እኔም ምስ​ክር እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ፤ ከእኔ በፊት አም​ላክ አል​ነ​በ​ረም፤ ከእ​ኔም በኋላ አይ​ኖ​ርም።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ የሚ​ቤ​ዥም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እን​ዲህ ይላል፥ “እኔ ፊተኛ ነኝ፤ እኔም ኋለኛ ነኝ፤ ከእኔ ሌላም አም​ላክ የለም።


አሁ​ንም አንቺ ቅም​ጥል ተዘ​ል​ለሽ የም​ት​ቀ​መጪ፥ በል​ብ​ሽም፥ “እኔ ነኝ ከእ​ኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበ​ለ​ትም ሆኜ አል​ኖ​ርም፤ የወ​ላድ መካ​ን​ነ​ት​ንም አላ​ው​ቅም” የም​ትዪ፥ ይህን ስሚ፤


የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ሽ​ንም ሥጋ​ቸ​ውን ይበ​ላሉ፤ እንደ ጣፋጭ ወይን ጠጅም ደማ​ቸ​ውን ጠጥ​ተው ይሰ​ክ​ራሉ፤ ሥጋ ለባ​ሹም ሁሉ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ት​ሽና ታዳ​ጊሽ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብን ኀይል የም​ደ​ግፍ እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


እኔም በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል እን​ዳ​ለሁ፥ እኔም አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ቤም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም።


በም​ዕ​ራብ ያሉት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም፥ በፀ​ሐይ መው​ጫም ያሉት ክብ​ሩን ይፈ​ራሉ። መቅ​ሠ​ፍ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ እንደ ኀይ​ለኛ ፈሳሽ በቍጣ ይመ​ጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios