ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ፥ ቃሏን ከምታለዝብ ከሌላዪቱ ክፉ ሴት፥ የሕፃንንነት ባልዋን ከምትተው፥ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከምትረሳ፤ ይጠብቅህ ዘንድ፤
ኢዩኤል 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ልጅነት ባልዋ ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ድንግል አልቅሺ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልጅነት ዕጮኛዋን እንዳጣች ድንግል፣ ማቅ ለብሳችሁ አልቅሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጮኛዋ ስለሞተባት ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ድንግል አልቅሺ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እጮኛዋ ስለ ሞተባት ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ልጃገረድ እናንተም አልቅሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቍንጅናዋ ባል ማቅ ለብሳ እንደምታለቅስ ድንግል አልቅሺ። |
ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ፥ ቃሏን ከምታለዝብ ከሌላዪቱ ክፉ ሴት፥ የሕፃንንነት ባልዋን ከምትተው፥ የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ከምትረሳ፤ ይጠብቅህ ዘንድ፤
እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ደንግጡ፤ ሴቶች ሆይ፥ እዘኑ፤ ልብሳችሁንም አውልቁ፤ ዕራቁታችሁንም ሁኑ፤ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ።
ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፤ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል፤ ካህናቷም ያለቅሳሉ፤ ደናግሎችዋም ተማረኩ፤ እርስዋም በምሬት አለች።
ዓመት በዓላችሁንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማሬያችሁንም ወደ ዋይታ እለውጣለሁ፤ ማቅንም በወገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃነትንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመጣለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደርጋችኋለሁ፤ ከእርሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆናሉ።
እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድር ነው? ዘር አይደለምን? ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።