ኢዮብ 8:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኀጢአተኞች እንዲሁ ይጠፋሉና፤ ሌሎችም ከመሬት ይበቅላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ሕይወቱ በዚህ ያከትማል፤ ሌሎች አትክልትም ከመሬት ይበቅላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ የመንገዱ ደስታ እንዲህ ነው፥ ሌሎችም ከመሬት ይበቅላሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አረሙም በዚህ ዐይነት ይደርቃል፤ ሌሎች አትክልቶችም ከመሬት ያቈጠቊጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ የመንገዱ ደስታ እንዲህ ነው፥ ሌሎችም ከመሬት ይበቅላሉ። |
እነሆ፥ እግዚአብሔር የዋሁን ሰው አይጥለውም፥ የኀጢኣተኞችንም እጅ አያበረታም። የዝንጉዎችንም መባ አይቀበልም።
የዱር ዛፎች ሁሉ፥ ረዥሙን ዛፍ ዝቅ ያደረግሁ፥ አጭሩንም ዛፍ ከፍ ያደረግሁ፥ የለመለመውንም ዛፍ ያደረቅሁ፥ የደረቀውንም ዛፍ ያለመለምሁ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ተናገርሁ፤ እኔም አደረግሁ።”
በልባችሁም ‘አብርሃም አባት አለን’ እንደምትሉ አይምሰላችሁ፤ እላችኋለሁና ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ሊያስነሣለት እግዚአብሔር ይችላል።
ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።