Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 8:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 አረሙም በዚህ ዐይነት ይደርቃል፤ ሌሎች አትክልቶችም ከመሬት ያቈጠቊጣሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነሆ፤ ሕይወቱ በዚህ ያከትማል፤ ሌሎች አትክልትም ከመሬት ይበቅላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እነሆ፥ የመንገዱ ደስታ እንዲህ ነው፥ ሌሎችም ከመሬት ይበቅላሉ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ኀጢ​አ​ተ​ኞች እን​ዲሁ ይጠ​ፋ​ሉና፤ ሌሎ​ችም ከመ​ሬት ይበ​ቅ​ላሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እነሆ፥ የመንገዱ ደስታ እንዲህ ነው፥ ሌሎችም ከመሬት ይበቅላሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 8:19
8 Referencias Cruzadas  

የክፉ ሰው ድንፋታ ለአጭር ጊዜ ነው፤ እግዚአብሔርንም የሚክዱ ሰዎች ደስታቸው በቅጽበት የሚጠፋ ነው።


“እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን አይጥላቸውም፤ ክፉዎችንም አይረዳቸውም።


ድኾችን ከትቢያ ችግረኞችንም ከዐመድ ቊልል ያነሣቸዋል።


በአንዱ ላይ የሚፈርድ፥ ሌላውን ነጻ የሚያወጣ፥ ትክክለኛ ፈራጅ እግዚአብሔር ነው።


በምድሪቱ ያሉ ዛፎች ሁሉ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ፤ እኔ ረጃጅም ዛፎችን አሳጥራለሁ፤ አጫጭር ዛፎችንም ከፍ ብለው እንዲያድጉ አደርጋለሁ፤ እኔ ለምለም ዛፎችን አደርቃለሁ፤ ደረቅ ዛፎችንም አለመልማለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ አደርጋለሁ ያልኩትንም ሁሉ እፈጽማለሁ።”


‘እኛ የአብርሃም ልጆች ነን’ በማለት የምታመልጡ አይምሰላችሁ፤ እግዚአብሔር ከነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆችን ሊያስነሣለት ይችላል እላችኋለሁ።


እርሱ ድኾችን ከትቢያ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ያደርጋቸዋል፤ የክብርም ዙፋን ያወርሳቸዋል የምድርን መሠረቶች የሠራ እግዚአብሔር ነው፤ በእነርሱም ላይ ዓለምን የፈጠረ እርሱ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos