ቦታው ቢውጠው፦ እንደዚህ ያለ አላየሁም ብሎ ይክደዋል።
ከስፍራው ሲወገድ ግን፣ ያ ቦታ ‘አይቼህ አላውቅም’ ብሎ ይክደዋል።
ከቦታው ቢጠፋ፦ አላየሁህም ብሎ ይክደዋል።
አንድ ሰው ከቦታው ቢነቅለው የነበረበት ቦታ አይታወቅም።
እነሆ ተደላድያለሁ በሚልበት ጊዜ ለዘለዓለም ይጠፋል። የሚያውቁትም ወዴት ነው? ይላሉ።
ዐይን አየችው፤ ነገር ግን ዳግመኛ አታየውም፤ ስፍራውንም ከእንግዲህ ወዲህ አያውቀውም።
ወደ ቤቱም ዳግመኛ አይመለስም፥ ስፍራውም ዳግመኛ እርሱን አያውቀውም።
የሚያየኝ ሰው ዐይን ከእንግዲህ ወዲህ አያየኝም፤ ዐይንህ በእኔ ላይ ይሆናል፤ እኔም አልገኝም።
በድንጋይ ክምር ላይ ያድራል፤ በድንጋዮቹም መካከል ይኖራል።
የዱር ዛፎች ሁሉ፥ የተከልኸው የሊባኖስ ዝግባም ይጠግባሉ።
ልቤ ደነገጠብኝ፥ ኀይሌም ተወኝ፥ የዐይኖቼም ብርሃን ፈዘዘብኝ።